Saturday, May 17, 2014

‪‎አዛንና ኢቃም‬



1. እውነተኛና ታማኝ ሊሆን ይገባል፡፡ ምክንያቱም ሰዎች ለሰላትና ለፆም የሚመረኮዙት በመሆኑ እንዲህ ካልሆነ በአዛኑ ሊያሳስታቸው ይችላል::
2. አቅመ አዳም የደረሰና አእምሮ ጤናማ መሆን አለበት፡፡ ነገር ግን የሚለይ ህፃን ልጅ አዛን ቢል ትክክል ይሆናል፡፡
3. የሰላት ወቅቶችን የሚያውቅ መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም የመጀመሪዎች መቅቶችን እየተጠባበቀ አዛን ስለሚያደርግ ነው:: የማያውቅ ከሆነ ግን ሊሳሳት ወይም ሊያበላሽ ይችላል::
4. ድምፁ ከፍተኛ ሆኖ ሰዎችን ሊያሰማ የሚችል መሆን አለበት፡፡
5. ከትልቁም ሆነ ከትንሹ ሀደስ የፀዳ መሆን አለበት፡፡
6. ቆሞ ወደ ቂብላ በመዞር አዛን ማድርግ አለበት፡፡
7. ጣቶችን ጆሮው ውስጥ ከትቶ
“حي على الصلاة” ሲል ወደ ቀኝ
“حي على الفلاح” ሲል ደግሞ ወደ ግራ እየዞረ ማድረግ አለበት፡፡
8. አዛንን ቀስ እያለና ክፍተት እየፈጠረ ኢቃምን ደግሞ እያፋጠነና እያከታተለ ማድግ አለበት፡፡
በሀዲስ ጥቅሶች የተዘገቡ የአዛንና የኢቃም አደራረጐች ብዙ ናቸው፡፡ ከነዚህም ውሰጥ ነብዩ (ﷺ) ለአቢ መህዙር የአስተማሩት አደራረግ እንደሚከተለው ነው፡፡
“አሏሁ አክበር አሏሁ አክበር አሏሁ አክበር አሏሁ አክበር፣
አሽሐዱ አንላኢላሃ ኢለሏህ አሽሐዱ አንላኢላሃ ኢለሏህ
አሽሐዱ አነ ሙሐመደ ረሱላሏህ አሽሐዱ አነ ሙሐመደ ረሱላሏህ
ሀየ ዓለ ሰላት ሀየ ዓለ ሰላት
ሀየ ዓለል ፈላህ ሀየ ዓለል ፈላህ
አሏሁ አክበር አሏሁ አክበር
ላኢላሃ ኢለላህ”
የኢቃም አደርረግ‬ ደግሞ
“ አሏሁ አክበር አሏሁ አክበር፣
አሽሐዱ አንላኢላሃ ኢለሏህ
አሽሐዱ አነ ሙሐመደ ረሱላሏህ
ሀየ ዓለ ሰላት
ሀየ ዓለል ፈላህ
ቀድ ቃመቲ ሰላት ቀድ ቃመቲ ሰላት
አሏሁ አክበር አሏሁ አክበር ላኢላሃ ኢለላህ”
ለዚህ ማሰረጃው አነስ ባስተላለፉት ሀዲስ እንዲህ ብለዋል
“ቢላል አዛን ሲያደርግ ጥንድ ጥንድ እንዲያደርግ ኢቃም ሲያደርግ ደግሞ “ቀድ ቃመቲ ሰላት” ሲቀር ሌሎችን በነጠላ እንዲያደርግ ታዟል፡፡”(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
ይህ የአዛንና የኢቃም አደራረግ ቢላል ከነብዩ (ﷺ) ሀገሩ ጉዞም ላይ ሲሆን የሚያደርገው በመሆኑ የተወደደ አደራረግ ነው፡፡ አዛን ሲደረግ በተርጂዕ(አዛን ላይ የምስክር ቃሎችን ሲናገር አስቀድሞ ለራሱ ብቻ በሚሰማ መልኩ ካለ በኋላ በመጮህ መድገም ነው፡፡) ኢቃም ደግሞ በጥንድ ቢደረግ ችግር የለውም፡፡ ምክንያቱም እንዲህ አይነቱ ልዩነቶች የተፈቀዱ ናቸው፡፡ የሱብሂ አዛን ላይ “ሀየ አለል ፈላህ” ከተባለ በኋላ “አሰላቱ ኸይሩ ሚነ ነውም” ሁለት ጊዜ ማለት ሱና ነው፡፡ምክንያቱም አቡ መህዙም ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል:- “ለሱብሂ ሰላት አዛን ስታደርግ “አሰላቱ ኸይሩ ሚነ ነውም” በል፡፡”

ከ  www.facebook.com/easyfiqh  የተወሰደ።

No comments:

Post a Comment