Saturday, February 6, 2016

የቁርኣን ሰዎች

ከ ወንድም Ibnu Munewor የተወሰደ።

ሸይኽ ሳሊሕ አልፈውዛን እንዲህ ይላሉ: "የቁርኣን ሰዎች ሲባል የሚፈለገው የሚያፍዙት፣ በሥርዓት የሚያነቡት ወዘተ ••• ማለት አይደለም። የቁርኣን ሰዎች የሚባሉት ባያፍዙት እንኳን የሚሰሩበት ናቸው። እነዚያ ትእዛዛቱን የሚፈፅሙ፣ ክልከከላውን የሚርቁ፣ ከወሰኑ የሚቆሙ እነሱ ናቸው የቁርኣን ሰዎች። እነዚህ የአላህ ሰዎች ናቸው፣ ከፍጡሩ ልዩዎቹ! ቁርኣንን አፍዞ፣ አሳምሮ የሚቀራና ሑሩፎቹን አስተካክሎ እያነበበ ነገርግን ድንጋጌዎችቹን የሚጥስ የሆነ ሰው ይሄ የቁርኣን ሰው አይደለም። ከአላህ ልዩ ሰዎች ውስጥም አይደለም። ይልቁንም ይሄ አላህና መልእክተኛውን የሚያምፅ ቁርኣንንም የሚፃረር ነው። አዎ።
የቁርኣን ሰዎች በተጨማሪ እነዚያ ማስረጃ የሚያደርጉት ናቸው። በማስረጃ አጠቃቀም ላይ በሱ ላይ ሌላን የማያስቀድሙ ናቸው። ፊቅሁንም አሕካሙንም በጥቅሉ ዲናቸውንም ከሱ ይወስዳሉ። እነዚህ ናቸው የቁርኣን ሰዎች።
【ሸርሑ ኪታቢ አልዑቡዲያህ】

ከ ወንድም Ibnu Munewor የተወሰደ።

No comments:

Post a Comment