Thursday, May 15, 2014

መፋቂያ... ተወደጅ ሱና!

መፋቂያ... ተወደጅ ሱና!

መፋቂያ መጠቀም በየትኛውም ወቅት ሱና (የተወደደ) ነው፡፡

قال رسول الله صلى الله عليه وسلم : "السواك مطهرة للفم، مرضاة للرب" علقه البخاري في صحيحه، وإسناده صحيح (الإرواء 1/105).
📈
ነብዩ () እንዲህ ብለዋል:- “መፋቂያ አፍን የሚያፀዳና አላህንም የሚያስወድድ ነው፡፡ቡኻሪ ሙዓለቅ አድርገው ዘግበውታል።ሰነዱ ሰሂህ ነው።አልባኒ አልـኢርዋእ 1/105
  عن  أبي هريرة رضي الله عنه أن النبي صلى الله عليه وسلم قال : " لولا أن أشق على أمتي لأمرتهم بالسواك عند كل صلاة" رواه البخاري ومسلم. وفي رواية للبخاري: "عند كل وضوء".
📈
እንዲህም ብለዋል:- “ለህዝቦቼ ማስቸገር ባይሆንብኝ ለእያንዳንዱ ሰላት መፋቂያ እንዲጠቀሙ አዛቸው ነበር፡፡ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ሌላኛው የቡኻሪ ዘገባ   «በየውዱእ ወቅቱ» ይላል።

አል ኢማም አነወዎይ መፋቂያ ሱና ለመሆኑ የኢስላም ሊቃውንትን የአንድነት አቋም በማሰባሰብ "ኢጅማዕ" እንዳለበት ገልጸዋል።
 ጥርስን መፋቅ ይበልጥ የሚወደድባቸው ወቅቶች፤

በየትኛውም ወቅት መፋቂያን መጠቀም የተወደደ ሱና ነው፡፡
ፆመኛም ጠዋትም ይሁን ከቀትር በኋላ ጥርሱን ቢፍቅ ችግር የለውም፡፡ ምክንያቱም ነብዩ () ጥርስ መፋቅን ሲያስተምሩ አንዱን ወቅት ከሌላው አልለዩም፡፡
ይሁንና መፋቂያን መጠቀም በተለይ በነዚህ ወቅቶች ይበልጥ የተወደደ ነው፡፡
ውዱእ በሚደረግበት ጊዜ፣ 
የአፍ ጠረን ሲለወጥ፣
ቁርአን ለመቅራትና ዚክር ለማድረግ ሲፈልግ፣ 
ሰላት ለመስገድ፣ 
መስጂድ ሲገባ፣
ወደቤት ሲገባ፤ለዚህም መረጃው፤
ثبت من حديث عائشة رضي الله عنها أنها سئلت : بأي شيء يبدأ رسول الله صلى الله عليه وسلم إذا دخل بيته ، قالت : "كان إذا دخل بيته بدأ بالسواك" رواه مسلم


ሚቅዳም ኢብኑ ሹረይህ እንዳስተላለፈው አባቱ ነብዩ () ቤት ሲገቡ በምን እንደሚጀምሩ ዓኢሻን ጠይቋቸው ሲመልሱ፤ጥርሳቸውን በመፋቅ፡፡ብለዋል:: (ሙስሊም ዘግበውታል)
ለረዥም ሰዓት በዝምታ ሲቆይና ጥርስ ሲበልዝም ይበልጥ ይወደዳል፤
ለሊት ከእንቅልፍ ሲነቁ፤
عن حذيفة بن اليمان رضي الله عنه قال: كان النبي صلى الله عليه وسلم إذا قام من الليل يشوص فاه بالسواك" رواه البخاري ومسلم ومعنى: يشوص فاه، أي يغسله ويدلكه.

ነብዩ(ﷺ) ሌሊት ሲነሱ አፋቸውን በመፋቂያ ያፀዱ ነበር”(ሙስሊም ዘግበውታል)
ወደ አምልኮ ሲገባና ወደ አላህ ሲቃረብ በፀዳና ባማረ ሁኔታ መገኘት ይጠበቅበታል፡፡
አላህ በትምህርቱ የምንጠቀምና እየተረሳ ያለውን የጠበቀ የነብዩ ()ሱናህ የምንተገብር ያድርገን። 
አሚን!!
🔈 ውድ አንባቢ! አንባቢ ብቻ ሳይሆን ተሳታፊም ይሆኑ ዘንድ መፋቂያ (ሲዋክ) መጠቀም ከሚወደድባቸው ወቅቶች መካከል ቢያንስ አንዱን ይጥቀሱ::

No comments:

Post a Comment