Friday, May 23, 2014

ሓዲስ ቁጥር 3



ከአነስ ኢብኑ ማሊክ እንደተዘገበው ነብዩ (صلى الله عليه وسلم) እንዲህ ብለዋል
‹‹ሶስት ባህሪዎች ያሉት በነሱ ምክንያትየኢማን ጥፍጥና ያገኛል፡፡ አላህና መልዕክተኛውን ከማንም ይበልጥ መውደድ : አንድን ሰው ለማንም ሳይሆን ለአላህ ብቻ ብሎ መውደድ : አላህ ከክህደት ካወጣው በኃላ ዳግም ወደ ክህደት መመለስን እሳት ውስጥ እንደመወርወር መጥላት›› (ቡኻሪና ሙስሊም)
ሐዲሡን የዘገቡት ሶሓባ አጭር ታሪክ
ስማቸው፡- አነስ ኢብኑ ማሊክ አል አንሳሪ
ከታሪካቸው፡- ነብዩ (صلى الله عليه وسلم) ወደ መዲና ከተሰደዱ ጀምሮ ለአስር አመታት ነብዩን (صلى الله عليه وسلم)ሲያገለግሉ ቆይተዋል በመሆኑም ከነብዩ (صلى الله عليه وسلم) ብዙ አውቀቶችን ወርሰዋል፡፡
ዕለተ ህልፈት፡- በስተመጨረሻ እድሜያቸው ወደ በስራ ከተማ ዲንን ለማስተማር ተጉዘው እዚያው ከቆዩ በኃላ በ93ኛው አመተ ሒጅራ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል፡፡

የሐዲሱ ትምህርቶች
1.ኢማን በትክክለኛ የአላህ ባህሪዎች የሚቀመስ ጥፍጥና አለው ፡፡ 2.አላህና መልዕክተኛውን ከማንም ይበልጥ መውደድ የኢማን ከፍተኛ ደረጃ ነወ፡፡ 3.ውዴታ (አላህና መልዕክተኛውን መውደድ) ከኢባዳ ዘርፎች አንዱ ነው፡፡ 4.ሙስሊም ወንድምን ለአላህ ብሎ መውደድ ከኢማን ክፍል አንዱ ነው፡፡ 5.ኢስላም የእርስ በእርስ መዋደድንና ትስስርን ያበረታታል፡፡ 6.ክህደትንና ከሀዲያንን መጥላት ከኢማን ክፍል ይመደባል፡፡ 7.ውዴታ ደረጃዎች አሉት በመሆኑም ከፍተኛ የውዴታ ደረጃ ለአላህ ብቻ ማድረግ ግዴታ ነው ፡፡ 8.ቁርአንና ሐዲስን ከመመሪያዎች ሁሉ ማስቀደም አላህንና መልዕክተኛውን ከመውደድ ውስጥ ይመደባል፡፡
የተወሰደ ።

No comments:

Post a Comment