Friday, May 30, 2014

Hadith ቁጥር 4 ‪ልብን ማጥራትና ስራን ማሳመር




Hadith ቁጥር 4

 
ከአቡ ሑረይራ እንደተዘገበው የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል ‹‹አላህ ወደመልካችሁና ወደ ገንዘቦቻችሁ አይመለከትም ነገር ግን ወደ ልቦቻችሁና ወደ ስራዎቻችሁ ይመለከታል ፡፡ (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል) 

1.ከሰዎች የሚፈለገው ትልቁ ነገር የፀዳ ልብና ያማረ ተግባር ነው፡፡
2.ልብን ማፅዳት ማለት ከሽርክ ፣ ከምቀኝነት ፣ በሰዎች ከመመካት ፣ ሙስሊምን ከመጥላትና ከመሳሰሉት የልብ በሽታዎች መጠበቅ ማለት ሲሆን ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ልብ ካማረ አካል ሙሉ ያምራል ብለዋል፡፡
3.ስራ ተቀባይነት የሚኖረው ለአላህ ብቻ ጥርት ተደርጎ ሲሰራና የነብዩን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) መመሪያ የተከተለ ሲሆን ብቻ ነው፡፡
4.መልካም ስራን ማብዛት አላህ ዘንድ ደረጃን ከፍ ያደርጋል፡፡
5.ሰዎች የሚለኩት በውበትና በገንዘብ ሳይሆን ለአላህ ባላቸው ፍራቻና መልካም ስራ ነው፡፡
6.አላህ ሀብት የሰጠው ሰው ሀብቱን በመልካም ነገር ላይ ካላዋለው አላህ ዘንድ ይጠየቅበታል፡፡
7.ሙስሊም ገንዘብ ስሌለለው መናቅ ወይም ገንዘቡ ብሎ ማክበር የሙስሊም ባህሪ አይደለም


የተወሰደ።

Tuesday, May 27, 2014

ከአርበዒን አን-ነወውያህ ሓዲሶች የምንወስዳቸው ትምህርቶች 2ኛ እና 3ኛ ሓዲስ የሃይማኖት ደረጃዎች።



2ኛ እና 3ኛ  ሓዲስ

የሃይማኖት ደረጃዎች።

ከሁለተኛው እና  ከሶስተኛው ሓዲስ የምንወስዳቸው ትምህርቶች

1.      ሙስሊሞች ጋር መቀላቀልና ለነሱ ደግሞ መልካም ባህርያትን ማሳየት እንዳለብን
2.     ሌሎች ሰዎችን ለማስተማር ብሎ ዓሊምን መጠየቅ እንደሚቻልና ይህንን ያደረገ ደግሞ ልክ እውቀቱን የሚያሰተላልፈው ሰው አጅር ያገኛል።
3.     እስልምና  አምስት ማእዘናት እንዳሉት። ካለነሱ ደግሞ ዲን እንደማይቆም።
4.     ኢማን ስድስት ማእዘናት እንዳሉት።
5.     እስልምናና ኢማን አብረው ሲጠቀሱ የተለያየ ትርጉም እንዳላቸው። ለየብቻቸው ሲጠቀሱ ግን አንደኛው ሌላኛውን አጠቃሎ እንደሚይዝ።
6.     የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ሶስት ደረጃዎች እንዳላቸው። እነሱም
ኢስላም(ሙስሊም)
ኢማን(ሙእሚን)
ኢሕሳን(ሙሕሲን)

7.     የውመል ቂያማ ሰአቷ የተወሰነ እንደሆነ እና እሷንም የሚያቃት አንድ አላህ ብቻ እንደሆነ። ምልክቶችም እንደላት።

Sunday, May 25, 2014

ከአርበዒን አን-ነወውያህ ሓዲሶች የምንወስዳቸው ትምህርቶች ሓዲስ 1ኛ

1ኛ  ሓዲስ

ስራ በንያ ነው የሚለካው።

ከአንደኛው ሓዲስ የምንወስዳቸው ትምህርቶች
1.      ሁሉም ስራ ንያ እንዳለው።
2.     ሁሉም ሰው በንያው መሰረት ስራው እንደሚመዘንለት።

3.     የሚያስተምር ሰው ምሳሌን እያጠቀሰ ቢያስተምር ጥሩ እንደሆነ።

Friday, May 23, 2014

ሓዲስ ቁጥር 3



ከአነስ ኢብኑ ማሊክ እንደተዘገበው ነብዩ (صلى الله عليه وسلم) እንዲህ ብለዋል
‹‹ሶስት ባህሪዎች ያሉት በነሱ ምክንያትየኢማን ጥፍጥና ያገኛል፡፡ አላህና መልዕክተኛውን ከማንም ይበልጥ መውደድ : አንድን ሰው ለማንም ሳይሆን ለአላህ ብቻ ብሎ መውደድ : አላህ ከክህደት ካወጣው በኃላ ዳግም ወደ ክህደት መመለስን እሳት ውስጥ እንደመወርወር መጥላት›› (ቡኻሪና ሙስሊም)
ሐዲሡን የዘገቡት ሶሓባ አጭር ታሪክ
ስማቸው፡- አነስ ኢብኑ ማሊክ አል አንሳሪ
ከታሪካቸው፡- ነብዩ (صلى الله عليه وسلم) ወደ መዲና ከተሰደዱ ጀምሮ ለአስር አመታት ነብዩን (صلى الله عليه وسلم)ሲያገለግሉ ቆይተዋል በመሆኑም ከነብዩ (صلى الله عليه وسلم) ብዙ አውቀቶችን ወርሰዋል፡፡
ዕለተ ህልፈት፡- በስተመጨረሻ እድሜያቸው ወደ በስራ ከተማ ዲንን ለማስተማር ተጉዘው እዚያው ከቆዩ በኃላ በ93ኛው አመተ ሒጅራ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል፡፡

የሐዲሱ ትምህርቶች
1.ኢማን በትክክለኛ የአላህ ባህሪዎች የሚቀመስ ጥፍጥና አለው ፡፡ 2.አላህና መልዕክተኛውን ከማንም ይበልጥ መውደድ የኢማን ከፍተኛ ደረጃ ነወ፡፡ 3.ውዴታ (አላህና መልዕክተኛውን መውደድ) ከኢባዳ ዘርፎች አንዱ ነው፡፡ 4.ሙስሊም ወንድምን ለአላህ ብሎ መውደድ ከኢማን ክፍል አንዱ ነው፡፡ 5.ኢስላም የእርስ በእርስ መዋደድንና ትስስርን ያበረታታል፡፡ 6.ክህደትንና ከሀዲያንን መጥላት ከኢማን ክፍል ይመደባል፡፡ 7.ውዴታ ደረጃዎች አሉት በመሆኑም ከፍተኛ የውዴታ ደረጃ ለአላህ ብቻ ማድረግ ግዴታ ነው ፡፡ 8.ቁርአንና ሐዲስን ከመመሪያዎች ሁሉ ማስቀደም አላህንና መልዕክተኛውን ከመውደድ ውስጥ ይመደባል፡፡
የተወሰደ ።

Wednesday, May 21, 2014

የሰላት ወቅቶች። የዙህር ወቅት፣ የዐስር ሰላት ወቅት


የሰላት ወቅቶች

ግዴታ የሆኑ ሰላቶች በሀያ አራት ሰዐት ውስጥ አምስት ሲሆኑ ለእያንዳንዱ ሰላት የተወሰኑ ወቅቶች አሏቸው፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፡-
‹‹ሶላት በምእምናን ላይ በጊዜያት የተወሰነች ግዴታ ናትና፡፡›› (አል ኒሳእ:1ዐ3)
በመሆኑም ወቅቱ ሳይደርስ የሚሰገድ ሰላት ተቀባየይነት የለውም፡፡ 
ስለ ሰላት ወቅት ከሚጠቅሱ ሀዲሶች ዋናው ኢብኑ ዑመር ያስተላለፉት ሀዲስ ሲሆን
ነብዩ (ﷺ)እንዲህ እንዳሉ አስተላልፈውልናል :-

“የዙህር ወቅት ፀሐይ ወደ ምዕራብ ዘንበል ካለችበት ሰዓት ጀምሮ የአንድ ሰው ጥላ ከቁመቱ እኩል ሊሆን ትንሽ እስኪቀረው ድረስ ነው፡፡ 
የዓስር ወቅት ደግሞ የፀሐይ ጥላ ከአንድ ሰው ቁመት እኩል ከሚሆንበት ሰዓት ጀምሮ ፀሐይ ደብዘዝ እስክትል:: 
የመግሪብ ወቅት ፀሐይ ከጠለቀችበት ሰዓት ጀምሮ የሰማይ ደንገዝገዝ እስኪሰወር:: 
የዒሻ ወቅት ደግሞ እስከ እኩለ ለሊት ድረስ ሲሆን 
የሱብሂ ሰላት ወቅት ደግሞ ጐህ ከቀደደ ጀምሮ ፀሐይ ልትወጣ ትንሽ እስከሚቀራት ድረስ ነው፡፡”(ሙስሊም ዘግበውታል)

የዙህር ወቅት
የዙህር ወቅት ፀሐይ ከእኩለ ሰማይ ወደ ምዕራብ ዘንበል ስትል ጀምሮ የአንድ ነገር ጥላ ከርዝመቱ እኩል እስከሚሆን ድረስ ሲሆን በመጀመሪያው ወቅት ላይ መስገድ ግን የተወደደ ነው፡፡ ነገር ግን ጠራራ ፀሐይ ከሆነ ትንሽ በረድ እስከሚል ድረስ ማዘግየት የበለጠ ይወደዳል፡፡ ነብዩ እንዲህ ብለዋል 
“ሙቀት ከፍተኛ ሲሆን ትንሽ በረድ አድርጋችሁ ዙህርን ስገዱ ከፍተኛ ሙቀት የጀሀነም እንፋሎት ነው፡፡”(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

የዐስር ሰላት ወቅት
የዐስር ሰላት ወቅት የአንድ ነገር ጥላ ከቁመቱ እኩል ከሆነበት ማለትም ከዙህር ማብቂያ ወቅት ጀምሮ ፀሐይ ሊጠልቅ ትንሽ እስከሚቀረው ድረስ ሲሆን ዐስርንም በመጀመሪያው ወቅት መስገድ ሱና ነው፡፡ እንዲያውም መካከለኛይቱ ሰላት በማለት አላህ እንዲህ ሲል የገለፀው ነው፡-
‹‹በሶላቶች (በተለይ) በመካከለኛይቱም ሶላት ላይ ተጠባበቁ፡፡ ታዛዦች ኾናችሁም ለአላህ ቁሙ፡፡›› (አል በቀራህ 238)
ነብዩም (ﷺ) እንድንከባከበው እንዲህ በማለት አዘዋል 
“የዐስር ሰላት ያመለጠው ቤተሰቦቹንና ንብረቱን እንዳጣ ነው፡፡”(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል) 
በሌላም ሀዲስ እንዲህ ብለዋል
“የዐስር ሰላትን የተወ ሰው ስራው ይታበስበታል፡፡”( ቡኻሪ ዘግበውታል)

የዕለቱ ጥያቄ ይሳተፉ
የዓስር ወቅት መቼ ነው?




ከ www.facebook.com/easyfiqh የተወሰደ።

Tuesday, May 20, 2014

የዑምራ አፈፃፀም ስርዓት




የዑምራ አፈፃፀም ስርዓት

1. ወደ ሚቃት በምትደርስበት ጊዜ እራስህን ማፅዳት፣ መታጠብ እና ከኢሕራም ልብስህ ውጪ አካልህን ሽቶ መቀባት ሱና ይሆንልሀል፡፡ በመቀጠልም የኢሕራም ልብስህን ሽርጥና ኩታህን (ሽርጥህን በማሸረጥ ኩታህን በማጣፋት) ልበስ።(የኢሕራም ልብሶችህን በተመለከተ)የተሻለ የሚሆነው ሁለቱም ነጭ መሆናቸው ነው፡፡ ሴት ልጅን በተመለከተ እስካልተገላለጠች፣ ከወንዶች እና ከካፊሮች ጋር በአለባበስ እስካልተመሳሰለች የፈለገችውን ልብስ ትለብሳለች፡፡ ከዚህ በኋላ ለዑምራ
لبيك عمرة
لَبَّيْكَ اللَّهُمَّ لَبَّيْكَ لَبَّيْكَ لاَشَرِيكَلَكَ لَبَّيْكَ إِنَّ الْحَمْدَ وَالنِّعْمَةَ لَكَ وَالْمُلْكَ لاَشَرِيكَ لَكَ
“ለበይከ ዑምረተን”
“ለበይክ አላሁመ ለበይክ ለበይከ ላ ሸሪከ ለከ ለበይክ፣ ኢነልሀምደ ወኒዕመተ ለከ ወልሙልክ ላ ሸሪከ ለክ” በማለት ኒያ (ኢሕራም) ታደርጋለህ፡፡
ትርጉሙም፦ «አቤት አላህ ሆይ!አሁንም አቤት የዑምራን ስርአት ለመፈፀም(ተዘጋጅቻልሁ)። አቤት አላህ ሆይ! አሁንም አቤት ለአንተ አጋር የለህም። ምስጋና፣ፀጋና ንግስናም ለአንተ ነው። አጋር የለህም።» (ቡኻሪ እና ሙስሊም የዘገቡት)
ከዚህ በላይ የተጠቀሰውን (ተልቢያን) በማለት ላይ ወንዶች ድምፃቸውን ከፍ ሲያደርጉ ሴቶች ግን ድምፃቸውን ከፍ አያደርጉም፡፡ ኒያን ካደረግክበት ሰዓት አንስቶም ተልቢያውን ሌሎች ዚክሮችን እና አላህን ምህረት መጠየቅን (እስቲግፋርን) ታበዛለህ፡፡
2. መካ በምትደርስበትም ወቅት ከሀጀረል-አስወድ ጀምረህ “አላሁ አክበር” በማለት በካዕባ ዙሪያ ሰባት ዙር ጠዋፍ አድርግ፡፡ በዚህም ወቅት አላህን ማውሳት እንዲሁም ከተደነገጉ የዚክር እና የዱዓእ አይነቶች በፈለግከው እርሱን መለመን ትችላለህ፡፡ በሩክነል የማኒ እና በሀጀረል-አስወድ መካከል ስትሆን የሚከተለውን ማለትህ (ዱዓእ ማድረግህ) ሱንና ነው። 
رَبَّنَا آتِنَا فِي الدُّنْيَا حَسَنَةً وَفِي الْآخِرَةِ حَسَنَةً وَقِنَا عَذَابَ النَّارِ
“ረበና አቲና ፊዱንያ ሀሰነተን ወፊል አኺረቲ ሐሰነተን ወቂና ዓዛበ-ንናር” 
ትርጉሙም፡- «ጌታችን ሆይ! በምድረ ዓለም ደግን ነገር (ጸጋን) በመጨረሻይቱም አገር ደግን ነገር (ገነትን) ስጠን፤ የእሳትንም ቅጣት ጠብቀን» {አል-በቀራ፡201}
ከዚህ በኋላ ከተመቸ እርቀት ላይ ብትሆን እንኳ ከመቃመ-ኢብራሂም ኋላ፣ካልሆነም በመስጂዱውስጥ በማንኛውም ስፍራ (ሁለት ረከዓ) ትሰግዳለህ፡፡
በዚህኛው ጠዋፍ ለወንድ ልጅ ኢድጢባዕ (ማለትም የኩታውን መሀል በቀኝ እጁ ብብት ስር፤ ጫፎቹን ደግሞ በማጣፋት ግራ ትከሻው ላይ ማድረግ) እንዲሁም በጠዋፉ የመጀመሪያ ሦስት ዙሮች ላይ ብቻ ረምል (እርምጃን ከማቀራረብ ጋር መፍጠን) ሱንና ነው፡፡
3. በመቀጠልም ወደ ሰፉ ኮረብታ በመሄድ (ወደርሱ ስትቀርብ) ይህንን የአላህ ቃል አንብብ፦
ﭧﭨﭽﮅﮆﮇﮈﮉﮊﮋﮌﮍﮎﮏﮐﮑﮒﮓﮔﮕﮖﮗﮘﮙﮚﮛﮜﮝﮞﮟﭼ البقرة: ١٥٨
ትርጉሙም፡- «ሶፋና መርዋ ከአላህ(ትዕዛዝ መፈጸሚያ) ምልክቶች ናቸው፡፡ ቤቱን (ካዕባን) በሐጅ ወይም በዑምራህ ሥራ የጎበኘ (ያቀደ) ሰው በሁለቱ (መካከል) በመመላለሱ በርሱ ላይ ኃጢአት የለበትም፡፡ መልካምንም ሥራ በፈቃደኛነት የሠራ ሰው (አላህ ይመነዳዋል)፤ አላህ አመስጋኝ(የባሮቹንም ስራ)ዐዋቂ ነውና፡፡» {አል-በቀራ፡158}
በላዩም ላይ ወጥተህ ወደ ካዕባ አቅጣጫ በመዞር ሶስት ጊዜ “አልህምዱሊላህ አላሁ አክበር” በማለት አላህን ከማመስገን ጋር አልቀው፣ ዱዓዕም የሚያደርግ ሰው እጁን እንደሚያነሳው እጅህን ከፍ አድርገህ ሶስት ጊዜ
"لاَإِلَهَ إِلاَّاللَّهُ وَحْدَهُ لاَشَرِيكَ لَهُ لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ وَهُوَعَلَى كَلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَحْدَهُ أَنْجَزَ وَعْدَهُ وَنَصَرَ عَبْدَهُ وَهَزَمَ الأَحْزَابَ وَحْدَهُ"
“ላ ኢላሀ ኢለሏህ ወህደሁ ላ ሸሪከ ለሁ፤ ለሁል ሙሉኩ ወለሁል ሀምዱ ወሁወ አላኩሉ ሸይኢ ቀዲር”“ላ ኢላሀ ኢለሏህ ወህደሁ አንጀዘ ወዕደሁ ወነሰረ ዐብደሁ ወሀዘመል አህዛበ ወህደሁ” በል።
ትርጉሙም፦ « ከአላህ ሌላ አምልኮ የሚግባው አምላክ የለም። አንድ ነው አጋርም የለውም። ንግስና ለእርሱ የተገባ ነው። ምስጋናም ለእርሱ የተገባ ነው። እርሱ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነው። ከአላህ ሌላ አምልኮ የሚገባው አምላክ የለም። ቃልኪዳኑን ሞልቷል። ባሪያውንረድቷል።የተሰበሰበውንም የጠላት ጦር ለብቻው አንኮታኩቷል።» [ሙስሊም የዘገቡት]
ይህን ከማለትህም ጋር በየመሃሉ አላህን መማፀንህ ዱዐእህንም ሶስት ሶስት ግዜ ደጋግመህ ማድረግህ ሱንና ነው፡፡ ከዚህ በላይ ከተጠቀሱት ዚክሮች የተወሰኑትን ብቻ ብትልም ችግር የለውም፡፡
* ከዚያም ከሰፋ በመውረድ የዑምራህን ሰዕይ ሰባት ግዜ በሰፋና መርዋ መካከል አድርግ፡፡ በሁለቱ አረንጓዴ ምልክቶች መካከል ስትሆን የቻልከውን ያክል ትፈጥናለህ(ትሮጣለህ)፡፡ ከምልክቶቹ በፊት በተለመደው እርምጃህ ትራመድ እንደነበረው ሁሉከምልክቶቹም በኋላ በተለመደው እርምጃህ(ሰዕይህን)ቀጥለህ መርዋ ላይ ትወጣለህ፤ አላህን ታመሰግናለህ ልክ ሰፋ ላይ የፈፀምከውን ድርጊት ትፈፅማለህ፡፡
* ለጠዋፍ እና ሰዕይ የተለየ እንዲሁም ግዴታ የሆነ ዚክር የሌለ ሲሆን ይልቁኑ ጠዋፉን እና ሰዕዩን የሚፈጽመው ግለሰብ ከነብዩ () በትክክለኛ ሰነድ ለተዘገቡት ዚክሮች እና ዱዓዋች ትኩረት ከመስጠት ጋር ከዚክር እና ዱዓዕ አልያም ቁርዓንን ከማንበብ የገራለትን ይፈፅማል፡፡ 
4. ሰዕይህን በተሟላ መልኩ ከጨረስክፀጉርህን ተላጨው ወይም አሳጥረው ሆኖም ሙተመተዕ ከሆንክ መላጨትህን ከሐጅ ተሀሉል ለምታደርግበት ወቅት አቆይተኸው ለአሁኑ ፀጉርህን ማሳጠርህ በላጭ ነው፡፡ በዚህ ተግባርህ ዑምራህ የተሟላ ይሆናል፡፡ ከዚህ በኋላ (ሙተመቲዕ ከሆንክ ነው ) በኢሕራም የተነሳ የተከለከልካቸው ነገሮች (መሕዙራቱል-ኢሕራም) ሁሉ ይፈቀዱልሃል።
* በተጨማሪም ሙተመተዕ ወይም ቃሪን ከሆንክ አንድ በግ (ፍየል) በግልህአልያም ከግመል እና በሬ አንዱን ለሰባት በእርዱ ዕለት (ከዚያም በኋላ ባሉ ሶስት ተከታታይ ቀናት) ማረድ ግዴታ ሲሆንብህ ይህንን ማድረግ ካልቻልክ አስር ቀን (ሶስቱን በሐጅ ላይ ሰባቱን ወደ ቤተሰቦችህ ስትመለስ) መፆም ግዴታ ይሆንብሀል፡፡

Sunday, May 18, 2014

ሰላት


Photo: ‎ትምህርት ቁጥር 36

#ሰላት

ሚያዝያ 13/8/2006 

ግዴታ ስለመሆኑ፡-
ሰላት ግዴታ መሆኑ በቁርአን በሀዲስና በዑለማዎች ስምምነትም (ኢጅማዕ) የተረጋገጠ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፡-
‹‹ሶላትንም ደንቡን ጠብቃችሁ ስገዱ፡፡›› (አል በቀራህ 43)
በዚህ መልኩ በብዙ አንቀፆች ላይ ተናግሯል፡፡
በሌላም አንቀፅ አላህ እንዲህ ብሏል፡-
‹‹ለእነዚያ ላመኑት ባሮቼ በእርሱ ውስጥ ሽያጭና ወዳጂነት የሌለበት ቀን ከመምጣቱ በፊት ሶላትን በደንቡ ይሰግዳሉ፡፡›› (አል ኢብራሂም 31)

ከሀዲስ ማስረጃዎች ውሰጥም ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል
 “ሰላቶች አምሰት ምንዳቸው ግን ሀምሳ ነው፡፡”(ቡኻሪ ዘግበውታል)
ቡኻሪና ሙሰሊም በዘገቡት ሀዲስ ስለ ኢስላም ለጠየቃቸው ግለሰብ እንዲህ ብለውታል
 “በቀንና በሌሊት ውስጥ አምስት ሰላቶችን መስገድ…” ጠያቅውም ከዚህ ሌላ አለብኝን? ሲላቸው አይ በራስህ ፈቃድ ከሰገድክ እንጂ ሌላ ግዴታ ሰላት የለምብህም ብለውታል፡፡”

ሰላት ግዴታ የሚሆነው አቅመ አዳም በደረሰና አእምሮ ጤናማ በሆነ ሙስሊም ላይ ሲሆን ካፊር ህፃንና እብድ ላይ ግዴታ አይደለም፡፡ ነብዩ እንዲህ ብለዋል
 “ከሶስት ሰዎች ብዕር ተነስቷል (ወንጀል አይፃፍባቸውም ማለት ነው) የተኛ እስኪነቃ፣ እብድ እስኪድንና ህፃን እስኪደርስ፡፡” 

ህፃን ሰባት አመት ሲሞላው ሶላት እንዲሰግድ መታዘዝ ሲኖርበት አስር አመት ሞልቶት ማይሰግድ ከሆነ ደግም በመግረፍ እንዲሰግድ ማድረግ ግዴታ ነው፡፡ የሰላትን ግዴታነት የካደ ወይም የማይሰግድ በዚህ ተግባሩ ከእስልምና ይወጣና ከሀዲ ይሆናል፡፡ 
ነብዩ እንዲህ ብለዋል
 “በእኛና በእነርሱ መካከል ያለው መለያ ሰላት ነው እሱን የተወ በእርግጥ ክዷል፡፡”                 (ሙስሊም ዘግበውታል)
#ሊንኩን_በመጫን_ፔጁን_ላይክ(like) _ያድርጉ =====>
--------------------------------
www.facebook.com/easyfiqh
--------------------------------
ኢንሻ አላህ ጠቃሚ ኢስላማዊ ዕውቀትን ይገበዩበታል!!! 

ሼር ማድረግ እንዳይረሱ‎


ግዴታ ስለመሆኑ፡-
ሰላት ግዴታ መሆኑ በቁርአን በሀዲስና በዑለማዎች ስምምነትም (ኢጅማዕ) የተረጋገጠ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፡-
‹‹ሶላትንም ደንቡን ጠብቃችሁ ስገዱ፡፡›› (አል በቀራህ 43)
በዚህ መልኩ በብዙ አንቀፆች ላይ ተናግሯል፡፡
በሌላም አንቀፅ አላህ እንዲህ ብሏል፡-
‹‹ለእነዚያ ላመኑት ባሮቼ በእርሱ ውስጥ ሽያጭና ወዳጂነት የሌለበት ቀን ከመምጣቱ በፊት ሶላትን በደንቡ ይሰግዳሉ፡፡›› (አል ኢብራሂም 31)

ከሀዲስ ማስረጃዎች ውሰጥም ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል
“ሰላቶች አምሰት ምንዳቸው ግን ሀምሳ ነው፡፡”(ቡኻሪ ዘግበውታል)
ቡኻሪና ሙሰሊም በዘገቡት ሀዲስ ስለ ኢስላም ለጠየቃቸው ግለሰብ እንዲህ ብለውታል
“በቀንና በሌሊት ውስጥ አምስት ሰላቶችን መስገድ…” ጠያቅውም ከዚህ ሌላ አለብኝን? ሲላቸው አይ በራስህ ፈቃድ ከሰገድክ እንጂ ሌላ ግዴታ ሰላት የለምብህም ብለውታል፡፡”

ሰላት ግዴታ የሚሆነው አቅመ አዳም በደረሰና አእምሮ ጤናማ በሆነ ሙስሊም ላይ ሲሆን ካፊር ህፃንና እብድ ላይ ግዴታ አይደለም፡፡ ነብዩ እንዲህ ብለዋል
“ከሶስት ሰዎች ብዕር ተነስቷል (ወንጀል አይፃፍባቸውም ማለት ነው) የተኛ እስኪነቃ፣ እብድ እስኪድንና ህፃን እስኪደርስ፡፡” 

ህፃን ሰባት አመት ሲሞላው ሶላት እንዲሰግድ መታዘዝ ሲኖርበት አስር አመት ሞልቶት ማይሰግድ ከሆነ ደግም በመግረፍ እንዲሰግድ ማድረግ ግዴታ ነው፡፡ የሰላትን ግዴታነት የካደ ወይም የማይሰግድ በዚህ ተግባሩ ከእስልምና ይወጣና ከሀዲ ይሆናል፡፡ 
ነብዩ እንዲህ ብለዋል
“በእኛና በእነርሱ መካከል ያለው መለያ ሰላት ነው እሱን የተወ በእርግጥ ክዷል፡፡” (ሙስሊም ዘግበውታል)


ከ www.facebook.com/easyfiqh የተወሰደ።

Saturday, May 17, 2014

‪‎አዛንና ኢቃም‬



1. እውነተኛና ታማኝ ሊሆን ይገባል፡፡ ምክንያቱም ሰዎች ለሰላትና ለፆም የሚመረኮዙት በመሆኑ እንዲህ ካልሆነ በአዛኑ ሊያሳስታቸው ይችላል::
2. አቅመ አዳም የደረሰና አእምሮ ጤናማ መሆን አለበት፡፡ ነገር ግን የሚለይ ህፃን ልጅ አዛን ቢል ትክክል ይሆናል፡፡
3. የሰላት ወቅቶችን የሚያውቅ መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም የመጀመሪዎች መቅቶችን እየተጠባበቀ አዛን ስለሚያደርግ ነው:: የማያውቅ ከሆነ ግን ሊሳሳት ወይም ሊያበላሽ ይችላል::
4. ድምፁ ከፍተኛ ሆኖ ሰዎችን ሊያሰማ የሚችል መሆን አለበት፡፡
5. ከትልቁም ሆነ ከትንሹ ሀደስ የፀዳ መሆን አለበት፡፡
6. ቆሞ ወደ ቂብላ በመዞር አዛን ማድርግ አለበት፡፡
7. ጣቶችን ጆሮው ውስጥ ከትቶ
“حي على الصلاة” ሲል ወደ ቀኝ
“حي على الفلاح” ሲል ደግሞ ወደ ግራ እየዞረ ማድረግ አለበት፡፡
8. አዛንን ቀስ እያለና ክፍተት እየፈጠረ ኢቃምን ደግሞ እያፋጠነና እያከታተለ ማድግ አለበት፡፡
በሀዲስ ጥቅሶች የተዘገቡ የአዛንና የኢቃም አደራረጐች ብዙ ናቸው፡፡ ከነዚህም ውሰጥ ነብዩ (ﷺ) ለአቢ መህዙር የአስተማሩት አደራረግ እንደሚከተለው ነው፡፡
“አሏሁ አክበር አሏሁ አክበር አሏሁ አክበር አሏሁ አክበር፣
አሽሐዱ አንላኢላሃ ኢለሏህ አሽሐዱ አንላኢላሃ ኢለሏህ
አሽሐዱ አነ ሙሐመደ ረሱላሏህ አሽሐዱ አነ ሙሐመደ ረሱላሏህ
ሀየ ዓለ ሰላት ሀየ ዓለ ሰላት
ሀየ ዓለል ፈላህ ሀየ ዓለል ፈላህ
አሏሁ አክበር አሏሁ አክበር
ላኢላሃ ኢለላህ”
የኢቃም አደርረግ‬ ደግሞ
“ አሏሁ አክበር አሏሁ አክበር፣
አሽሐዱ አንላኢላሃ ኢለሏህ
አሽሐዱ አነ ሙሐመደ ረሱላሏህ
ሀየ ዓለ ሰላት
ሀየ ዓለል ፈላህ
ቀድ ቃመቲ ሰላት ቀድ ቃመቲ ሰላት
አሏሁ አክበር አሏሁ አክበር ላኢላሃ ኢለላህ”
ለዚህ ማሰረጃው አነስ ባስተላለፉት ሀዲስ እንዲህ ብለዋል
“ቢላል አዛን ሲያደርግ ጥንድ ጥንድ እንዲያደርግ ኢቃም ሲያደርግ ደግሞ “ቀድ ቃመቲ ሰላት” ሲቀር ሌሎችን በነጠላ እንዲያደርግ ታዟል፡፡”(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
ይህ የአዛንና የኢቃም አደራረግ ቢላል ከነብዩ (ﷺ) ሀገሩ ጉዞም ላይ ሲሆን የሚያደርገው በመሆኑ የተወደደ አደራረግ ነው፡፡ አዛን ሲደረግ በተርጂዕ(አዛን ላይ የምስክር ቃሎችን ሲናገር አስቀድሞ ለራሱ ብቻ በሚሰማ መልኩ ካለ በኋላ በመጮህ መድገም ነው፡፡) ኢቃም ደግሞ በጥንድ ቢደረግ ችግር የለውም፡፡ ምክንያቱም እንዲህ አይነቱ ልዩነቶች የተፈቀዱ ናቸው፡፡ የሱብሂ አዛን ላይ “ሀየ አለል ፈላህ” ከተባለ በኋላ “አሰላቱ ኸይሩ ሚነ ነውም” ሁለት ጊዜ ማለት ሱና ነው፡፡ምክንያቱም አቡ መህዙም ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል:- “ለሱብሂ ሰላት አዛን ስታደርግ “አሰላቱ ኸይሩ ሚነ ነውም” በል፡፡”

ከ  www.facebook.com/easyfiqh  የተወሰደ።

Friday, May 16, 2014

ነብዩ (صلى الله عليه وسلم) መታዘዝ!


ነብዩ (صلى الله عليه وسلم) መታዘዝ!

ከአቡ ሁረይራ እንደተዘገበው የአላህ መልዕክተኛ (صلى الله عليه وسلم) እንዲህ ብለዋል
‹‹ ሁሉም ህዝቦቼ ጀነተን ይገባሉ እምቢ ያለሲቀር የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ማነው እምቢ የሚል ሲላቸው፡- እሳቸውም አሉ “የታዘዘኝ ጀነት ገባ እኔን ያመፀ ደግሞ በዕርግጥ እምቢ አለ”›› (ቡኻሪ ዘግበውታል)
ሐዲሡን የዘገቡት ሶሓባ አጭር ታሪክ
‪#‎ስማቸው‬:-አብዱራህማን ኢብኑ ሶኽር ይባላል፡፡አቡ ሑረይራ በሚሠኘው የቅፅል መጠሪያቸው ይታወቃሉ::
‪#‎ከታሪካቸው‬ :-በ7ኛው አመተ ሂጅራ ኢስላምን ተቀበሉ ከነብዩ (صلى الله عليه وسلم) የማይለዩ ስለነበሩ እጅግ በጣም ብዙ ሐዲሶችን በቃላቸው በመሸምደድ ለተተኪው ትውልድ ያስተላለፉ ታላቅ ሶሃቢ ለመሆን በቅተዋል ፡፡ ነብዩ የእውቀት ባለቤት እንዲሆኑ ዱዓ ያደርጉላቸው ስለነበር ታላቅን እውቀት የተጎናፀፉ ነበሩ፡፡
‪#‎ዕለተ_ህልፈት‬:-በ57ኛው አመተ ሂጅራ ነበር
1. ነብዩን (صلى الله عليه وسلم) መታዘዝና እሳቸውን መመሪያ መከተል አማራጭ የሌለው ግዳጅ ነው፡፡
2.የነብዩን (صلى الله عليه وسلم) መመሪያ መከተል የጀነት መግቢያ ምክንያት ነው፡፡
3.ነብዩን (صلى الله عليه وسلم) ማመፅ የጀሀነም መግቢያ ምክንያት ነው፡፡
4.ነብዩን (صلى الله عليه وسلم) መውደድ ማለት ለአላህ የምናደርገውን ኢባዳ (አምልኮ) በአጠቃላይ ከሳቸው በተማርነው መሰረት ብቻ ተፈጻሚ ማድረግ ነው፡፡
5.ነቢያችን (صلى الله عليه وسلم) ለዚህ ኡመት በጣም አዛኝ በመሆናቸው ሰዎች ጀነትንና ጀሀነምን የሚያስገባቸው ስራዎችን ከማመላከት አልተቆጠቡም፡፡
ጠቃሚ ኢስላማዊ ዕውቀትን ለማግኘት ይህን ፔጅ ላይክ (like) ያድርጉ:: 

Thursday, May 15, 2014

‎ኢስላማዊ የሂጃብ መስፈርቶች።


 ‎ኢስላማዊ የሂጃብ መስፈርቶች።

.
ስስ ሆኖ የሰውነት ከለርን ማሳየት የለበትም:: 
.
ወፍራምም ሆኖ የሰውነትን ቅርፅ የሚያስገምት መሆን የለበትም:: 
.
ያሸበረቀና እይታን የሚስብ መሆን የለበትም:: 
.
ዋጋው በጣም የተወደደ ዝናን ለማትረፍ የሚለበስ መሆን የለበትም:: 
.
ከወንዶች ልብስ ጋር መመሳሰል የለበትም:: 
.
ከኢስላም ሀይማኖት ውጪ ያሉ (የከሀዲዎችን) ልብስ መምሰል የለበትም:: 
.
ሙሉ የሰውነት ክፍልን መሸፈን አለበት::
    አላሁ (ሱብሃነሁ ወተአላ) ላይ ሴት ልጅን በሂጃብ ሲያዝ እንዲህ ብሏል -
وَلَا يُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ إِلَّا مَا ظَهَرَ مِنْهَا
«
ጌጣቸውንም ከእርሱ ግልጽ ከኾነው በስተቀር አይግለጡ፡፡»
 
እዚህ ጋር ታላቁ የተፍሲር ባለቤት ኢብኑ ከሲር ይህን አስመልክቶ ዓብደላህ ኢብን መስኡድ እንዲህ ማለቱን ተናግሯል። 
ይህ ማለት ልብሳቸውንና የሚያጣፉትን ማለት ነውበመቀጠልም ኢብኑ ዓባስና ተከታዮቹ ይህንን በፊትና መዳፎች እንደፈሰሩትም አስቀምጣል። 
 
ተፍሲር ኢብኑ ከሲር። 
  
ሸይኽ አብዱራህማን ቢን ናስር አስሰዕዲ አላህ ይዘንላቸውና ይህን አንቀጽ አስመልክተውም ሲተረጉሙ እንዲህ ብለዋል 
ማለትም ግልጹን ልብሱን ማለት ነው ፡፡ይህም በተለምዶ የሚለበሰው ነው ወደ መፈተን የማይጠራ እስከሆነ ድረስ
 
ሌላው እዚህ ጋር አላህ (ሱብሃነሁ ወተአላ) ግልጽ ከሆነው በስተቀር አለ እንጂ ግልጽ ካደረግነው በስተቀር አላለም፡:


www.nesiha.com  የተወሰደ።

መፋቂያ... ተወደጅ ሱና!

መፋቂያ... ተወደጅ ሱና!

መፋቂያ መጠቀም በየትኛውም ወቅት ሱና (የተወደደ) ነው፡፡

قال رسول الله صلى الله عليه وسلم : "السواك مطهرة للفم، مرضاة للرب" علقه البخاري في صحيحه، وإسناده صحيح (الإرواء 1/105).
📈
ነብዩ () እንዲህ ብለዋል:- “መፋቂያ አፍን የሚያፀዳና አላህንም የሚያስወድድ ነው፡፡ቡኻሪ ሙዓለቅ አድርገው ዘግበውታል።ሰነዱ ሰሂህ ነው።አልባኒ አልـኢርዋእ 1/105
  عن  أبي هريرة رضي الله عنه أن النبي صلى الله عليه وسلم قال : " لولا أن أشق على أمتي لأمرتهم بالسواك عند كل صلاة" رواه البخاري ومسلم. وفي رواية للبخاري: "عند كل وضوء".
📈
እንዲህም ብለዋል:- “ለህዝቦቼ ማስቸገር ባይሆንብኝ ለእያንዳንዱ ሰላት መፋቂያ እንዲጠቀሙ አዛቸው ነበር፡፡ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ሌላኛው የቡኻሪ ዘገባ   «በየውዱእ ወቅቱ» ይላል።

አል ኢማም አነወዎይ መፋቂያ ሱና ለመሆኑ የኢስላም ሊቃውንትን የአንድነት አቋም በማሰባሰብ "ኢጅማዕ" እንዳለበት ገልጸዋል።
 ጥርስን መፋቅ ይበልጥ የሚወደድባቸው ወቅቶች፤

በየትኛውም ወቅት መፋቂያን መጠቀም የተወደደ ሱና ነው፡፡
ፆመኛም ጠዋትም ይሁን ከቀትር በኋላ ጥርሱን ቢፍቅ ችግር የለውም፡፡ ምክንያቱም ነብዩ () ጥርስ መፋቅን ሲያስተምሩ አንዱን ወቅት ከሌላው አልለዩም፡፡
ይሁንና መፋቂያን መጠቀም በተለይ በነዚህ ወቅቶች ይበልጥ የተወደደ ነው፡፡
ውዱእ በሚደረግበት ጊዜ፣ 
የአፍ ጠረን ሲለወጥ፣
ቁርአን ለመቅራትና ዚክር ለማድረግ ሲፈልግ፣ 
ሰላት ለመስገድ፣ 
መስጂድ ሲገባ፣
ወደቤት ሲገባ፤ለዚህም መረጃው፤
ثبت من حديث عائشة رضي الله عنها أنها سئلت : بأي شيء يبدأ رسول الله صلى الله عليه وسلم إذا دخل بيته ، قالت : "كان إذا دخل بيته بدأ بالسواك" رواه مسلم


ሚቅዳም ኢብኑ ሹረይህ እንዳስተላለፈው አባቱ ነብዩ () ቤት ሲገቡ በምን እንደሚጀምሩ ዓኢሻን ጠይቋቸው ሲመልሱ፤ጥርሳቸውን በመፋቅ፡፡ብለዋል:: (ሙስሊም ዘግበውታል)
ለረዥም ሰዓት በዝምታ ሲቆይና ጥርስ ሲበልዝም ይበልጥ ይወደዳል፤
ለሊት ከእንቅልፍ ሲነቁ፤
عن حذيفة بن اليمان رضي الله عنه قال: كان النبي صلى الله عليه وسلم إذا قام من الليل يشوص فاه بالسواك" رواه البخاري ومسلم ومعنى: يشوص فاه، أي يغسله ويدلكه.

ነብዩ(ﷺ) ሌሊት ሲነሱ አፋቸውን በመፋቂያ ያፀዱ ነበር”(ሙስሊም ዘግበውታል)
ወደ አምልኮ ሲገባና ወደ አላህ ሲቃረብ በፀዳና ባማረ ሁኔታ መገኘት ይጠበቅበታል፡፡
አላህ በትምህርቱ የምንጠቀምና እየተረሳ ያለውን የጠበቀ የነብዩ ()ሱናህ የምንተገብር ያድርገን። 
አሚን!!
🔈 ውድ አንባቢ! አንባቢ ብቻ ሳይሆን ተሳታፊም ይሆኑ ዘንድ መፋቂያ (ሲዋክ) መጠቀም ከሚወደድባቸው ወቅቶች መካከል ቢያንስ አንዱን ይጥቀሱ::