Tuesday, March 15, 2016

9ኛ ሓዲስ:በአቅማችን ልክ እንደታዘዝን እና ልዩነትን ከማምጣት እንደተከለከልን።

الحديث التاسع

التكليف بما يستطاع والنهي عن الاختلاف

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ عَبْدِ الرَّحْمَنِ بْنِ صَخْرٍ  قَالَ: سَمِعْت رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ: "مَا نَهَيْتُكُمْ عَنْهُ فَاجْتَنِبُوهُ، وَمَا أَمَرْتُكُمْ بِهِ فَأْتُوا مِنْهُ مَا اسْتَطَعْتُمْ، فَإِنَّمَا أَهْلَكَ الَّذِينَ مِنْ قَبْلِكُمْ كَثْرَةُ مَسَائِلِهِمْ وَاخْتِلَافُهُمْ عَلَى أَنْبِيَائِهِمْ ".
رَوَاهُ الْبُخَارِيُّ [رقم:7288]، وَمُسْلِمٌ [رقم:1337].

9ኛ  ሓዲስ

የሓዲሱ ትርጉም

በአቅማችን ልክ እንደታዘዝን እና ልዩነትን ከማምጣት እንደተከለከልን።

አቡ ሁረይራ  የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلمእንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋሎህ አለ። “ የከለከልኳቹሁን ሁሉ ተከልከሉ። ካዘዝኳቹህ ውስጥ ደግሞ የቻላችሁትን ስሩ። ከናንተ በፊት የነበሩትን ህዝቦች ያጠፋቸውኮ ጥያቄ ማብዛታቸው እና ከብዮቻቸው መለያየታቸው ነው።”
ሓዲሱን ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

ከዘጠነኛው ሓዲስ የምንወስዳቸው ትምህርቶች

1. በቁርንአን እና በሓዲስ ከተከለከልነው ነገር መራቅ እንዳለብን።
2. በቁርአን እና በሓዲስ የታዘዝነውን ነገር የቻልነውን ያክል መስራት እንዳለብን።
3. ዲናችን(ሃይማኖታችን) ከአቅማችን በላይ የሆነን ነገር(የማንችለውን) እንድንሰራ እንደማያስገድደን።
4. የሚያስፈልገውን ጥያቄ ብቻ መጠየቅ እና ዝምብለን ጥያቄ ማብዛት እንደሌለብን(በተለይ ደግሞ በዋሒ ግዜ)።
5. ነብያት ላይ ጥያቄ ማብዛት እና ካመጡት ነገር መለየት(አለመከተል) ጥመትን እና ጥፋትን እንደሚያመጣ።

No comments:

Post a Comment