Thursday, February 26, 2015

በሒጃብሽ ላይ ፅናት ይኑርሽ!



www.facebook.com/tenbihat የተወሰደ።

በሒጃብሽ ላይ ፅናት ይኑርሽ!

﴿يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ قُل لِّأَزْوَاجِكَ وَبَنَاتِكَ وَنِسَاءِ الْمُؤْمِنِينَ يُدْنِينَ عَلَيْهِنَّ مِن جَلَابِيبِهِنَّ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَن يُعْرَفْنَ فَلَا يُؤْذَيْنَ ۗ وَكَانَ اللَّـهُ غَفُورًا رَّحِيمًا﴾
الأحزاب 59


«አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ
እንዲለቁ ንገራቸው፡፡ ይህ (በጨዋነታቸው) እንዲታወቁና 
(በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመኾን በጣም የቀረበ ነው፡፡ 
አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡» 
አል አህዛብ 59

ጅልባብ ማለት ሰውነትን በሙሉ ከላይ ጀምሮ የሚሸፍን ሰፊ የሆነ የልብስ አይነት ነው። አላህ ነብዩን ለሚስቶቻቸው ለልጆቻቸው እንዲሁም ለምእመናት በሙላ ጅልባቦቻቸውን በላያቸው ላይ በመልቀቅ ፊቶቻቸውንና ደረቶቻቸውን ይሸፍኑ ዘንድ እንዲነግሩ አዟቸዋል።

ሴት ልጅ ፊቷን ባእድ ከሆኑና ሙህርሟ ካልሆኑ ወንዶች የመሸፈን ግዴታ እንዳለባት ከቁርንአንና ከሱና የሆኑ ማስረጃዎች አመላክተዋል። አንዲት ሴት ሰውነቷን ከራሷ ጀምሮ እስከ እግሮቿ ድረስ እንድትሸፍን እንዲሁም በእግሯ ላይ ያደረገችው ጌጥ ድምፅ እንዳያሰማ በእግሯ መሬቱን እንዳትመታ ከታዘዘችና በዚህ መልኩ መሸፈን በሷ ላይ ግድ ከሆነ ፊቷን መሸፈኗ ደግሞ በበለጠ ሁኔታ ግድ እንደሚሆንባት ያስተዋይ አእምሮ ባለቤት አይጠራጠርም።

ይህም የሚሆነው ፊቷን በመክፈቷ ሊከሰት የሚችለው ፊትና ጸጉሯን በመክፈቷ ሊከሰት ከሚችለው ፊትና ወይንም የእግር ጥፍሮቿን በመክፈቷ ሊከሰት ከሚችለው ፊትና እጅግ የከበደ በመሆኑ ነው። የአንድ ሙእሚን ሰው አእምሮ የዚህን ሸሪአዊ ህግ ጥበብና ሚስጥር በሚያስተነትን ጊዜ ሴት ልጅ ጸጉሯን አንገቷን ክንዶቿን ባቷንና እግሮቿን ሸፍና እጆቿንና በውበት የተሞላ ፊቷን ከፍታ ትሄድ ዘንድ መፍቀዱ በፍጹም ከሸሪአዊው ጥበብ ጋር ተቃራኒ መሆኑን ያስተውላል።

በአሁን ዘመን ላይ ያለውን የሰዎችን ፊትን በመሸፈን ላይ ያለውን ቸልተኝነት በአንዳንድ ሙስሊም ሃገሮች ሴት ልጅ ከፊቷ ውጪ ያሉትን እንደ ራስ አንገት ደረትና ክንዶቿን ግልታ በየገበያው ላይ በግድ የለሽነት እንድትሄድ እንዳደረገት ያስተዋለ ሰው ሴት ልጅ ፊቷን እንድትሸፍን ያዘዛትን ሸሪአዊ ጥበብ ቁርጠኛ የሆነ ማወቅን ያውቃል።

አንቺ ሙስሊም ሴት ሆይ! አላህን በመፍራት ያንን ከፊትና የጸዳውንና ዋጅብ የሆነውን ከባለቤትና ሙህሪም ከሚሆኑ ወንዶች በስተቀር መላ ሰውነትን የሚሸፍነውን ሸሪአዊ ሂጃብ ልትለብሺ ይገባል። ሴት ልጅ ፊቷንና አንዳንድ የሰውነት ክፍሎቿን ባእድ ለሆኑ ወንዶች መግለጿን ባስተዋልን ጊዜ ብጣም ብዙ የሆኑ ጥፋቶችም ሰብስቦ ይዞ እናገኛለን።

በዚህ ነገር ውስጥ ጥቅም ሊኖር ይችላል ብንል እንኳን ይህ ጥቅም እጅግ በጣም ትንሽ በመሆኑ ከጥፋቶች ውስጥ ተከልሎ ሊታይ አይችልም።

አንዳንዶች የኒቃብን ሸሪዓዊ ብይን አስመልክቶ፤
"ዋጂብ ነው ወይስ መልበሱ በላጭ የሆነ (አፍደል)? " በሚል ጉንጭ አልፋ ክርክር ሴቶችን በማዋከብ ከኒቃብ ያርቃሉ።

ያንቺ አቋም የሚሆነው፤
☞ ዋጂብ ከሆነ መልበስ ግዴታዬን መወጣት ነው!
☞ ዋጂብ ያልሆነ ትርፍ ስራ ከሆነ ከማንም በላይ ወንጀሌን የሚያስምርና ደረጃዬን ከፍ የሚያደርግ መልካም ስራ ያስፈልገኛል የሚል ይሁን።

አላህ ሆይ!

ትክክለኛውን ኢስላማዊ ሂጃብ በመተግበር ላይ ፅናቱን ለግሰኝ!!

www.facebook.com/tenbihat የተወሰደ።

No comments:

Post a Comment