Tuesday, November 25, 2014

4ኛ ሓዲስ الحديث الرابع Amharic Arbeen hadith 4





الحديث الرابع

الخوف من سوء الخاتمة

عَنْ أَبِي عَبْدِ الرَّحْمَنِ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ مَسْعُودٍ قَالَ: حَدَّثَنَا رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم -وَهُوَ الصَّادِقُ الْمَصْدُوقُ-: "إنَّ أَحَدَكُمْ يُجْمَعُ خَلْقُهُ فِي بَطْنِ أُمِّهِ أَرْبَعِينَ يَوْمًا نُطْفَةً، ثُمَّ يَكُونُ عَلَقَةً مِثْلَ ذَلِكَ، ثُمَّ يَكُونُ مُضْغَةً مِثْلَ ذَلِكَ، ثُمَّ يُرْسَلُ إلَيْهِ الْمَلَكُ فَيَنْفُخُ فِيهِ الرُّوحَ، وَيُؤْمَرُ بِأَرْبَعِ كَلِمَاتٍ: بِكَتْبِ رِزْقِهِ، وَأَجَلِهِ، وَعَمَلِهِ، وَشَقِيٍّ أَمْ سَعِيدٍ؛ فَوَاَللَّهِ الَّذِي لَا إلَهَ غَيْرُهُ إنَّ أَحَدَكُمْ لَيَعْمَلُ بِعَمَلِ أَهْلِ الْجَنَّةِ حَتَّى مَا يَكُونُ بَيْنَهُ وَبَيْنَهَا إلَّا ذِرَاعٌ فَيَسْبِقُ عَلَيْهِ الْكِتَابُ فَيَعْمَلُ بِعَمَلِ أَهْلِ النَّارِ فَيَدْخُلُهَا. وَإِنَّ أَحَدَكُمْ لَيَعْمَلُ بِعَمَلِ أَهْلِ النَّارِ حَتَّى مَا يَكُونُ بَيْنَهُ وَبَيْنَهَا إلَّا ذِرَاعٌ فَيَسْبِقُ عَلَيْهِ الْكِتَابُ فَيَعْمَلُ بِعَمَلِ أَهْلِ الْجَنَّةِ فَيَدْخُلُهَا".
رَوَاهُ الْبُخَارِيُّ [رقم:3208]، وَمُسْلِمٌ [رقم:2643].


4ኛ ሓዲስ

የሓዲሱ ትርጉም

ከከፋ (መጥፎ) መጨረሻ መፍራት

ዓብደላህ ኢብን መስዑድ እንዲህ አለ። እውነት ተናጋሪ እና እውነት የተነገራቸው የአላህ መልእክተኛ እንዲህ አሉ። “ እያንዳንዳቹህ በእናቱ ሆድ ውስጥ ፍጥረቱ ይሰበሰባል። አርባ ቀን ንፍጥ የሚመስል ፈሳሽ ይሆናል። ከዛም የረጋ ደምን ይመስላል ለተመሳሳይ ግዜ (40 ቀን)። ከዛም የታኘከን ስጋ ይመስላል ለተመሳሳይ ግዜ (40 ቀን)። ከዛም መልእክተኛ ይላክና ሩሕ ይተነፍስበታል። መልእክተኛውም በአራት ነገሮች ላይ ይታዘዛል። ሲሳዩን፣ ፍጻሜውን፣ ስራውን፣ የተከፋ ወይንም ደስተኛ መሆኑን እንዲጽፍ ይታዘዛል። ከሱውጭ ሌላ በእውነት የሚመለክ አምላክ በሌለው ጌታ እምላሎህ ! አንዳቹህ በሱና በጀነት የስንዝር ያክል ርቀት እስከምትቀረው ድረስ የጀነት ሰዎችን ስራ ይሰራና ከዛም መጨረሻ ላይ መጽሃፉ ይቀድመውና የእሳት ሰዎችን ስራ ይሰራና እሳት ይገባል።ደግሞ አንዳቹህ በሱና በእሳት የስንዝር ያክል ርቀት እስከምትቀረው ድረስ የእሳት ሰዎችን ስራ ይሰራና ከዛም መጨረሻ ላይ መጽሃፉ ይቀድመውና የጀነት ሰዎችን ስራ ይሰራና ጀነት ይገባል።

ሓዲሱን ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

ከአራተኛው ሓዲስ የምንወስዳቸው ትምህርቶች

1. የሰው ልጅ ሆድ ውስጥ እያለ ለሱ የተመደበ መላኢካ እንዳለ።
2. የሰው ልጅ ሁኔታዎች፣ ሲሳዩ፣ ስራው፣ ፍጻሜው፣ ደስተኛ ነው ወይስ የተከፋ የሚለው ሁሉ ገና በናቱ ሆድ ውስጥ እያለ እንደተጻፈ።
3. በዚች ዓለም የሚከሰተው ክስተት ሁሉ በአላህ የተወሰነ እና ሁሉም ደግሞ ለውሑል መሕፉዝ ላይ የተጻፈነ እንደሆነ።
4. የሰው ልጅ እስኪሞት ድረስ አላህን በመፍራት ላይ መሆን እንዳለበት።
5. ከአላህ መከጀልን(መፈለግን) ማቋረጥ እንደሌለብን።
6. ለሰው ብለን አምልኮን ከመስራት መቆጠብ እንዳለብን። ለሰው ብሎ የሚሰራ ስራው መጨረሻ ላይ እንደሚበላሽበት።
7. ከ 4 ወር በፊት የወረደ ሰው እንዳልሆነ እና ከ 4 ወር ቡኋላ የወረደ ግን ልክ እንደ ማንኛውም ሙስሊም ተገንዞ፣ ሶላተል ጀናዛ ተሰግዶበት ሙስሊሞች ቀብር እንደሚቀበር።


No comments:

Post a Comment