Monday, July 18, 2016

" ስንቅና ሰናቂው"


🔘🔘🔘

" ስንቅና ሰናቂው"

ይቅርና መቶ — ደሞ ሁለት መቶ
አስር ሃያ ሚሊዮን—ሲባል ጆሮ ሰምቶ
ገርሞኝ ያስቀኛል —ቁጥሩ በ‘ጅግ በዝቶ
አስደንጋጩ አሃዝ —ለልቤ ተንዛዝቶ።

ናፍቆኝም አይደለ— ሆኖም አይደል ህልሜ
ሲጠራ ስሰማ— እንዲህ መደመሜ
ልፋቱ ገርሞኝ ነው —ሳይታክት መድከሙ
ዱንያን ለመሰብሰብ— እንዲህ መፋለሙ
ቀን ተሌት ሳይሰንፍ —አጥብቆ ማለሙ።
 ለዚህ ለጠፊ አለም— እንዲህ የታጠቀ
ለቀብሩም አስቦ —ስንቁን ከሰነቀ
ጀግንነት ነው መቸም —ብርቱ ጥንካሬ
እንዲህ ወንድም ሲገኝ —ባገር በመንደሬ።
ሸቀጡን ሲቃርም— እረፍት እየነሳው
ልቡን አስክሮለት— ቀብሩን ካረሳሳው
ይሄ ነው ደካማ— የንዋይ አምላኪ
የዱንያ ምርኮኛ —የሸቀጥ ሰባኪ!

በ ኡስታዝ መሐመድ ሲራጅ

➖➖➖