Wednesday, October 22, 2014

ድምጽ መቀየር





ሀምሌ 7/12/2006

ድምጽ መቀየር


አላህ (ሱብሃነሁ ወተአላ) ለምእመናን እናቶች እና እንዲሁም ከነርሱ በኃላ ለሚመጡት አማኝ ሴቶች እንዲህ ብሏል፤-
يَا نِسَاءَ النَّبِيِّ لَسْتُنَّ كَأَحَدٍ مِّنَ النِّسَاءِ ۚ إِنِ اتَّقَيْتُنَّ فَلَا تَخْضَعْنَ بِالْقَوْلِ فَيَطْمَعَ الَّذِي فِي قَلْبِهِ مَرَضٌ وَقُلْنَ قَوْلًا مَّعْرُوفًا [٣٣:٣٢]
« የነቢዩ ሴቶች ሆይ! ከሴቶች እንደማናቸው አይደላችሁም፡፡ አላህን ብትፈሩ (ትበልጣላችሁ)፡፡ያ በልቡ ውስጥ በሽታ ያለበት እንዳይከጅል በንግግር አትለስልሱም፡፡ መልካምንም ንግግር ተናገሩ፡፡ (33:32)
ድምጽ በተቃራኒ ጾታዎች መካከል ባለው ግንኙነት ከፍተኛ የሆነ ሳቢና ማግኔታዊ ሀይል አለው አንዱን ወደሌላው ጠልፎ የሚይዝ ልዩ ወጥመድ ነው:: አላህ (ሱብሃነሁ ወተአላ) አማኝ ሴት መልካምና ቁም ነገሮችን እንጂ ድምጽን በማለሳለስና በማቅለስለስ ወንዶችን ከማማለል እንድትታቀብ ከልክሏታል ፡፡ምክንቱም ይህ ሁኔታ በአዳማጯ ልብ ውስጥ በሽታን ይፈጥራልና ነው፡፡አዎ! ዝሙትን ያስናፍቃል። ለእርሱም ያነሳሳል ይገፋፋል። እዚህ ጋር የድምጽን የአቀየር ስልት በሁለት ከፍለን ልናየው እንችላለን ፡፡
1,ንግግሩን መቀየር ፡-ይህም ማለት አንዲት ሴት ተቃራኒ ጾታን በምታናግርበት ሰአት የተለያዩ የማቆላመጫ ቃላቶችን በመጠቀም ማናገር ነው::
ምሳሌ፡-እከልዬ ስሙን ጠርታ ፣ፍቅሬ ፣ህይወቴና ወዘተ... ይህ ሁኔታ በእውነቱ በቀጥታ መርዝ ነስናሽ አውዳሚ ነገር ነው::
2 በንግግር ውስጥ መለሳለስ፡- ይህ ደግሞ አንዲት ሴት ከተቃራኒ ጾታ ጋር መልካምና ቁም ነገር እያወራች ነገር ግን በውስጡ የምትጠቀማቸው የማለስለስ ፣የመጎተትና የመስለምለም ገጽታዎች ናቸው፡:
ለማንኛውም አንዲት አማኝ ከየትኛውም የፊትና ሙከራዎች አላህን (ሱብሃነሁ ወተአላ) ፈርታ እራሷን ልታቅብ ይገባል፡፡ምስጋና ለአላህ ተገባው፡፡ አትናገሪ አላላትም:: ነገር ግን ድምጷን ተገንና ግርዶ አድርጋ ወንዶችን የፈተናዋ ሰለባ እንዳታደርግ በአጽንኦ ከልክሏታል፡፡ በቃ እጥር ምጥን ቀልጠፍ ቆፍጠን ብሎ መልካምና ቁም ነገሮችን መናገር ዛዛታና እሰጣ ገባ አለመፍጠር:: ሌላው ቁም ነገር ደግሞ እስቲ አንቺ ውዲቷ እህቴ አስተውይ! አላህ እኮ ይህን የከለከለውን መጀመሪያ ያወረደው እጹብ ድንቅ የነብዩ (ﷺ) ሚስቶችና የአማኞች እናት በሆኑት እንስቶች ላይ ነው፡፡ታዲያ እኔና አንቺስ በምን መልኩ ነው መሆን የሚገባን??? እራስን መሸንገል አያዛልቅም:: ይልቁንም ያሉ ግድፈቶችንና መጥፎ ዝንባሌዎችን አርሞ ማስተካከል የብልህ ሰዎች መገለጫ ነው::