Wednesday, August 27, 2014

2ኛ ሓዲስ الحديث الثاني Amharic Arbeen hadith 2






الحديث الثاني

"مجىء جبريل ليعلم المسلمين أمر دينهم"

عَنْ عُمَرَ t أَيْضًا قَالَ: " بَيْنَمَا نَحْنُ جُلُوسٌ عِنْدَ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ذَاتَ يَوْمٍ، إذْ طَلَعَ عَلَيْنَا رَجُلٌ شَدِيدُ بَيَاضِ الثِّيَابِ، شَدِيدُ سَوَادِ الشَّعْرِ، لَا يُرَى عَلَيْهِ أَثَرُ السَّفَرِ، وَلَا يَعْرِفُهُ مِنَّا أَحَدٌ. حَتَّى جَلَسَ إلَى النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم . فَأَسْنَدَ رُكْبَتَيْهِ إلَى رُكْبَتَيْهِ، وَوَضَعَ كَفَّيْهِ عَلَى فَخْذَيْهِ، وَقَالَ: يَا مُحَمَّدُ أَخْبِرْنِي عَنْ الْإِسْلَامِ. فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم الْإِسْلَامُ أَنْ تَشْهَدَ أَنْ لَا إلَهَ إلَّا اللَّهُ وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللَّهِ، وَتُقِيمَ الصَّلَاةَ، وَتُؤْتِيَ الزَّكَاةَ، وَتَصُومَ رَمَضَانَ، وَتَحُجَّ الْبَيْتَ إنْ اسْتَطَعْت إلَيْهِ سَبِيلًا. قَالَ: صَدَقْت . فَعَجِبْنَا لَهُ يَسْأَلُهُ وَيُصَدِّقُهُ! قَالَ: فَأَخْبِرْنِي عَنْ الْإِيمَانِ. قَالَ: أَنْ تُؤْمِنَ بِاَللَّهِ وَمَلَائِكَتِهِ وَكُتُبِهِ وَرُسُلِهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ، وَتُؤْمِنَ بِالْقَدَرِ خَيْرِهِ وَشَرِّهِ. قَالَ: صَدَقْت. قَالَ: فَأَخْبِرْنِي عَنْ الْإِحْسَانِ. قَالَ: أَنْ تَعْبُدَ اللَّهَ كَأَنَّك تَرَاهُ، فَإِنْ لَمْ تَكُنْ تَرَاهُ فَإِنَّهُ يَرَاك. قَالَ: فَأَخْبِرْنِي عَنْ السَّاعَةِ. قَالَ: مَا الْمَسْئُولُ عَنْهَا بِأَعْلَمَ مِنْ السَّائِلِ. قَالَ: فَأَخْبِرْنِي عَنْ أَمَارَاتِهَا؟ قَالَ: أَنْ تَلِدَ الْأَمَةُ رَبَّتَهَا، وَأَنْ تَرَى الْحُفَاةَ الْعُرَاةَ الْعَالَةَ رِعَاءَ الشَّاءِ يَتَطَاوَلُونَ فِي الْبُنْيَانِ. ثُمَّ انْطَلَقَ، فَلَبِثْنَا مَلِيًّا، ثُمَّ قَالَ: يَا عُمَرُ أَتَدْرِي مَنْ السَّائِلُ؟. قَلَتْ: اللَّهُ وَرَسُولُهُ أَعْلَمُ. قَالَ: فَإِنَّهُ جِبْرِيلُ أَتَاكُمْ يُعَلِّمُكُمْ دِينَكُمْ ". رَوَاهُ مُسْلِمٌ [رقم:8] .

2ኛ ሓዲስ

የሓዲሱ ትርጉም

የእስልምና ሃይማኖት ደረጃዎች።

የሙእሚኖች መሪ የሆነው ዑመር ኢብኒ ኸጣብ እንዲህ አለ። “የሆነ ቀን ከአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] ጋር ተቀምጠን እያለ፡ በጣም ጥቁር ጸጉር ያለው፥ በጣም ነጭ ልብስ የለበሰ፥ የመንገደኛ ምልክት የማይታይበት፥ ከኛ ውስጥም ማንም የማያውቀው ሰውዬ ብቅ አለና እነብዩ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] ጋር ተቀመጠ። ጉልበቱን ከጉልበታቸው ጋር አገጣጠመ፥ መዳፉንም ታፋው ላይ አስቀመጠ። ከዛም አንተ ሙሓመድ ሆይ! ስለ ኢስላም ንገረኝ አላቸው። የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “ ኢስላም ማለት ፦ በእውነት የሚመለክ ጌታ አንድ አላህ ብቻ ነው ብሎ እና ሙሓመድም የአላህ መልእክተኛ ናቸው ብሎ መመስከር፣ ሶላትን በወቅቱና ቀጣይነት ባለው መልኩ መስገድ፣ ዘካን ማውጣት፣ ረመዳንን መጾም፣ የአላህ ቤትን ከቻልን መጎብኘት።” ሰውየውም “እውነት ተናገርክ” አለ። ዑመርም እንዲህ አለ “በሱ ተገረምን! እሳቸውን ይጠይቃል መልሶ እውነት ተናገርክ ይላቸዋል!” ከዛም ሰውየው ቀጠለና ስለ ኢማን ንገረኝ አላቸው። የአላህ መልእክተኛ[ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “ኢማን ማለት ፦ በአላህ ማመን፣ በመላኢኮች ማመን፣ በመጻህፍት ማመን፣ በመልእክተኞች ማመን፣ በመጨረሻው ቀን ማመን፣ በአላህ ውሳኔ ከፋም በጀም ማመን” ሰውየውም “እውነት ተናገርክ” አለ። ከዛም ሰውየው ቀጠለና ስለ ኢሕሳን ንገረኝ አላቸው። የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “ኢሕሳን ማለት አላህን እንደምታየው አድርገህ ልታመልከው ነው፥ አንተ ባታየውም እሱ ያየሃል እና።” ከዛም ሰውየው ቀጠለና የየውመል ቅያማ ሰአቷን ንገረኝ አላቸው። የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “ ተጠያቂው ከጠያቂው የበለጠ የሚያውቅ አይደለም” ከዛም ሰውየው ቀጠለና የየውመል ቅያማ ምልክቶቿን ንገረኝ አላቸው። የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “ ባርያ ጌታዋን ልትወልድ ነው፣ በባዶ እግራቸው የሚሄዱ፥ እርቃናቸውን የነበሩ፥ ድሆች የነበሩ የፍየል ጠባቂዎች ህንጻ ለመስራት ሲሽቀዳደሙ ልታይ ነው።” ከዛ ቡሃላ ሰውየው ሄደና ብዙ ቆየን። የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “አንተ ዑመር ሆይ!ጠያቂው ማን እንደሆነ ታውቃለህን?” ዑመርም “አላህና መልእክተኛው ያወቁ ናቸው።” በማለት መለሰ። የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “ የመጣው እኮ ጂብሪል ነው፥ ሃይማኖታቹህን ሊያስተምራቹህ መጣቹህ።”


ሓዲሱን ሙስሊም ዘግቦታል።




ከሁለተኛው ሓዲስ የምንወስዳቸው ትምህርቶች

1. ሙስሊሞች ጋር መቀላቀልና ለነሱ ደግሞ መልካም ባህርያትን ማሳየት እንዳለብን

2. ሌሎች ሰዎችን ለማስተማር ብሎ ዓሊምን መጠየቅ እንደሚቻልና ይህንን ያደረገ ደግሞ ልክ እውቀቱን የሚያሰተላልፈው ሰው አጅር ያገኛል።

3. እስልምና አምስት ማእዘናት እንዳሉት። ካለነሱ ደግሞ ዲን እንደማይቆም።

4. ኢማን ስድስት ማእዘናት እንዳሉት።

5. እስልምናና ኢማን አብረው ሲጠቀሱ የተለያየ ትርጉም እንዳላቸው። ለየብቻቸው ሲጠቀሱ ግን አንደኛው ሌላኛውን አጠቃሎ እንደሚይዝ።

6. የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ሶስት ደረጃዎች እንዳላቸው። እነሱም

ኢስላም(ሙስሊም)

ኢማን(ሙእሚን)

ኢሕሳን(ሙሕሲን)


7. የውመል ቂያማ ሰአቷ የተወሰነ እንደሆነ እና እሷንም የሚውያቃት አንድ አላህ ብቻ እንደሆነ። ምልክቶችም እንደላት።

Tuesday, August 19, 2014

‎ጥንብ_ነችና_ተዋት‬ !!!







ዘረኝነት በነብዩ ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም አንደበት “ጥንብ” እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ጥንብ ላይ የሚያንዣብበው ጥንብ አንሳ ነው!!!
ሰው ሁን ከጥንብ ራቅ፡፡ በተቅዋም ከፍ በል፡፡ “ከናተ በላጫችሁ ይበልጥ አላህን የሚፈራው ነው” ብሎናል ጌታችን ሱረቱል ሑጁራት ቁጥር፡ 13 ላይ፡፡ ሐበሻው፣ ጥቁሩ፣ ባሪያው ቢላል፤ ከዐረቡ፣ ከቁረይሹ፣ ከነብዩ ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም አጎት አቡ ለሀብ የመጠቀው በተቀዋው እንጂ በምንም አልነበረም፡፡ ሞኝ አትሁን:: ከእምነትህ ዘርህን አታስቀድም፡፡ አታይም እንዴ አላህ አረቡን፣ ቁረይሹን፣ የነብዩን ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም አጎት አቡ ለሀብን ከሀበሻው ጥቁር ባሪያ በታች ሲያደርገው?!!! መቼም አቡ ለሀብን የሚያወግዝ አንድ የቁርኣን ምእራፍ እንደወረደ የምትዘነጋው አይመስለኝም:: ቢላል ግን በኢማኑ ስንቶች የሚቋምጡበትን ማእረግ ነው የታደለው፡፡ የነብዩ ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም ቅርብ ሰው ነበር፡፡ የነብዩ ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም ሙአዚን መሆን ምንኛ መታደል ነው?!!! እርግጠኛ ነኝ ዛሬም ድረስ ቢላል በሙስሊሞች ልቦና ውስጥ ያለው ቦታ ታላቅ እንደሆነ እስክነግርህ አትጠብቀኝም፡፡
የትኛውንም ቋንቋ ስለተናገርክ ከማንም በላይ አይደለህም፡፡ ከየትኛውም ብሄር ስለመጣህም ከማንም በታች አይደለህም፡፡ ከሁሉ በፊት አንተ ለራስህ ትክክለኛ ቦታህን ስጥ፡፡ ሰዎች ስለሰቀሉህ አትሰቀልም፡፡ ሰዎች ስላወረዱህም አትወርድም፡፡ ለሆሳሱ ሁሉ ስላንተ እየመሰለህ አትሳቀቅ፡፡ ለቃላት መጥፎ ትርጉም እየሰጠህ አትሸማቀቅ፡፡ በትንሽ በትልቁ ውስጥህ አይደፍርስ፡፡ ጥቂት ከጠረጠርክ ሸይጣን ብዙ ያመሳስልብሃል፡፡ በዘሩ ሊኮፈስብህም የሚሻ ካለ፣ በማንነትህ ሊንቅህ ከዳዳው በተቅዋ ብለጠው፡፡ እሱ ጥንብ ቢያነሳ አንተም ጥንብ ታነሳለህ እንዴ?! እስቲ ማነው አህያ ጋዙን ለቀቀብኝ ብሎ እግሩን አንስቶ ጋዝ የሚለቅ? ምናልባት የማይረዳኝ ይኖር ይሆን? እንግዲያው እንዲህ ልበል:- እስቲ ማነው አህያ ፈሳብኝ ብሎ …
ሀላፊነት ይሰማህ፡፡ ቂል የዘረኝነት እሳት ሲያቀጣጥል አንተ ጋዝ አታርከፍክፍ፡፡ ቂል ትከተላለህ እንዴ? የአረሕማን ባሪያዎች ማለት ቂሎች በቂልኛ ሲያናግሯቸው በነገር ሲተነኩሷቸው ነገር እንዲበርድ የሚያደርጉ፣ ሠላም እንዲሰፍን የሚጥሩ ናቸው፡፡ ታዲያ አንተ የማን ባሪያ ነህና?! እርግጠኛ ነኝ “የሸይጣን ነኝ” አትለኝም!! የዘረኛ ዘረኝነት ዘረኛ አያድርግህ፡፡ የጥንብ አንሳው ጥንብ ማንሳት ጥንብ እንደማያስነሳህ ሁሉ፡፡ ሞኝ አትሁን! የሱ ዘረኝነት ላንተ ይቅርታ አይሆንም፡፡ እሱን ሸይጣን ቢጋልበው አንተም ጀርባህን ትሰጣለህ እንዴ? ግን የሸይጣን ፈረስ የሆነ ሰው ምንኛ አስቀያሚ ነው?!!! ያ ረቢ አንተ ጠብቀን፡፡ እናም እልሃለሁ ዘረኛው በቆሻሻ ዘረኝነት ውስጥ ሲዋኝ ብታየው ከቻልክ “አላህን ፍራ” በለው፡፡ በጥንብ እየተጨማለቀ እንደሆነም አስረዳው፡፡ ካልሆነልህ እሱ የያዘውን ጥንብ ለመንጠቅ እንዳትሞክር፤ ወይም ጥንብ ላይ እንዳትሻማ፡፡ ዘረኝነትን በዘረኝነት እንዳትመልስ፡፡ ሸይጣን ከፊት ሲስብህ፣ ከኋላም ሲገፋህ ዝም ብለህ አትነዳ፡፡ “አላህን ፍራ” ማለት ካቃተህ አላህን መፍራት ግን አያቅትህ፡፡ ሂሳብ ስራ ፈሪ ሁን!!! አዎ! አንድየውን፣ ሁሉን አዋቂ፣ ሁሉን ተመልካች፣ የፍርዱ ቀን ዳኛ… የሆነውን ጌታ የምትፈራ ሁን፡፡ አስተውል! “ፈሪ” እባላለሁ ብለህ አትጨነቅ፡፡ የፈራሀው አላህን እንጂ ሰው አይደለም! ቀድሞ ነገር አላህን እንደሚፈራ ሰው ጀግና አለና ነው? በጭራሽ!!! ነብዩስ ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም “ጀግና ማለት በንዴት ጊዜ ቁጣውን የሚውጥ ነው” አላሉም እንዴ? ታዲያ ትእዛዛቸውን እናክብራ! ወዳጅ ያምፃል እንዴ?!
የሌላውን ብሄር፣ ቋንቋ፣… ከማንቋሸሽ ራቅ፡፡ በሌላው ብሄር ላይ ከመሳለቅ ከመቀለድ ተጠንቀቅ፡፡ በሌላው ላይ ሲቀለድም አትሳቅ፡፡ ለራስህ የማትወደውን ነገር በሌላው ላይ አታድርግ፡፡ ይሄ ብዙዎቻችን የተለከፍንበት ገዳይ በሽታ ነው አላህ የጠበቀው ሲቀር፡፡ ምናልባት አንተ ስለራሰህ ደንታ ቢስ ሆነህ ሊሆን ይችላል፡፡ ግን ሁሉ እንዳንተ እንዳልሆነ አትርሳ፡፡
አትጠራጠር! ዘረኝነት የጃሂሊያ ስራ የመሀይሞች መታወቂያ እንደሆነ ታማኙ የአላህ መልእተኛ ነግረውሃል፡፡ ልብ በል! በምትናገረው ቋንቋ ከማንም በታች እንዳልሆንክ ሁሉ ከማንም በላይም አይደለህም! ከፍም ዝቅም የሚያደርግህ ስራህ እንጂ ዘርህ አይደለም፡፡ “ስራው ያስቀረውን ዘሩ አያስቀድመውም!!!” አይደል ያሉን ነብያችን ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም? ነብዩ እኮ ልጃቸው እንኳ “የነብይ ልጅ ነኝ” ብላ እንዳትሸወድ ይልቁንም በርትታ ሰርታ እራሷን እንድታተርፍ ነው አደራ ያሏት፡፡ ከፍ ማለት ከፈለግክ በኢስላም ከፍ በል፣ በተውሒድ ከፍ በል፣ በሱና ከፍ በል፡፡ ከዚህ በራቅክ ቁጥር እየወረደክ፣ እየዘቀጥክ፣ ቁልቁል እየተምዘገዝግክ እንደሆነ ነጋሪ እስኪነግርህ አትጠብቅ፡፡
ጥሪየ ማንነትህን እንድትጥል፣ ማንም በመታወቂያህ ሲረማመድ ዝም እንድትል አይደለም፡፡ ይልቁንም ጥሪየ አላህን እንድትፈራ ሚዛንህ እንድትጠብቅ ብቻ ነው፡፡ እናም የራስህን አስጠብቅ፣ ከሌሎች አትድረስ፡፡ ዘርህን ከእምነትህ ያስቀደምክ እለት ግን አትጠራጠር ታመሃል፡፡ እንዲህ እየገዘገዘህ ህመሙ ካልተሰማህማ ጭራሽ ቫይረሱ አናትህ ላይ ወጥቷል ማለት ነው፡፡ ጓደኛህ ይህን ህመምህን እያየ፣ ጥምብ ስታጨማልቅ እየተመለከተህ ዝም ካለህ፤ ወይ እንደ ተናካሽ ውሻ ያገኘኸውን ስለምትነክስ ፈርቶሃል፣ ወይ ደግሞ እሱም እንዳንተው ጥንብ አንሳ ነው ማለት ነው!!!
አደራ ግን እኔ ይሄን ሁሉ ስለቀልቅ ከችግሩ ነፃ ነኝ እያልኩ አይደለም፡፡ እኔ ቀርቶ ስንት ታላላቆች የሚወድቁበት ችግር እኮ ነው፡፡ ቀድሞ ነገር ታላቅ ሰው ማለት ፍፁም የማይሳሳት ነው እንዴ? ከስህተቱ የሚመለስ ነው እንጂ!!! እናም ቫይረሱ ጋር ላለመድረስ ስንሳሳትም ለመመለስ እንጣር፡፡ እንዲህም እንበል፡ “አላሁመ ኣቲ ነፍሲ ተቅዋሃ፣ ወዘኪሃ አንተ ኸይሩ መን ዘካሃ፣ አንተ ወሊየሃ ወመውላሃ!!!” “ጌታዬ ሆይ አንተ ለነፍሴ ተቅዋዋን ስጣት፡፡ አጥራትም፤ አንተ ከሚያጠራት ሁሉ በላጭ ነህና፡፡ አንተ ረዳቷም ተንከባካቢዋም ነህ”
-----------------
አንብበው ሲጨርሱ ‪#‎ሼር‬ ማድረጉን እንዳይረሱ

Tuesday, August 5, 2014

Amharic Arbeen hadith 1; 1ኛ ሓዲስ



بسم الله الرحمن الرحيم

الحديث الأول 
" إنما الأعمال بالنيات "
عَنْ أَمِيرِ الْمُؤْمِنِينَ أَبِي حَفْصٍ عُمَرَ بْنِ الْخَطَّابِ قَالَ: سَمِعْت رَسُولَ اللَّهِ يَقُولُ: " إنَّمَا الْأَعْمَالُ بِالنِّيَّاتِ، وَإِنَّمَا لِكُلِّ امْرِئٍ مَا نَوَى، فَمَنْ كَانَتْ هِجْرَتُهُ إلَى اللَّهِ وَرَسُولِهِ فَهِجْرَتُهُ إلَى اللَّهِ وَرَسُولِهِ، وَمَنْ كَانَتْ هِجْرَتُهُ لِدُنْيَا يُصِيبُهَا أَوْ امْرَأَةٍ يَنْكِحُهَا فَهِجْرَتُهُ إلَى مَا هَاجَرَ إلَيْهِ". 
رَوَاهُ إِمَامَا الْمُحَدِّثِينَ أَبُو عَبْدِ اللهِ مُحَمَّدُ بنُ إِسْمَاعِيل بن إِبْرَاهِيم بن الْمُغِيرَة بن بَرْدِزبَه الْبُخَارِيُّ الْجُعْفِيُّ [رقم:1]، وَأَبُو الْحُسَيْنِ مُسْلِمٌ بنُ الْحَجَّاج بن مُسْلِم الْقُشَيْرِيُّ النَّيْسَابُورِيُّ 
[رقم:1907] رَضِيَ اللهُ عَنْهُمَا فِي "صَحِيحَيْهِمَا" اللذِينِ هُمَا أَصَحُّ الْكُتُبِ الْمُصَنَّفَةِ.


1ኛ ሓዲስ
የሓዲሱ ትርጉም
ስራዎች ሁሉ የሚመዘኑት በንያ (ባሰብከው ሃሳብ) ነው።
ሁሉም ሰው (የነየተው ነገር) ያሰበው ነገር አለው።
የሙእሚኖች መሪ የሆነው ዑመር ኢብኒ ኸጣብ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋሎህ አለ። የአላህ መልእክተኛ እንዲህ አሉ። “ስራዎች ሁሉ የሚመዘኑት በንያ (ባሰብከው ሃሳብ) ነው። ሁሉም ሰው (የነየተው ነገር) ያሰበው ነገር አለው። ሰው ሁሉ ደግሞ (የነየተውን) ያሰበውን ያገኛል። ስደቱ ወደ አላህ እና ወደ መልእክተኛው ከሆነ፥ ስደቱ ወደ አላህ እና ወደ መልእክተኛው ይሆንለታል። ስደቱ ደግሞ ሊያገኛት ወደሚፈሊጋት አለም (ዱንያ) ወይንም ሊያገባት ወደሚፈልጋት ሴት ከሆነ፥ ስደቱ ወደተሰደተለት ምክንያት ይሆንለታል”
ሓዲሱን ቡኻሪና ሙስሊም ነው የዘገቡት።

ከአንደኛው ሓዲስ የምንወስዳቸው ትምህርቶች

1. ሁሉም ስራ ንያ እንዳለው።
2. ሁሉም ሰው በንያው መሰረት ስራው እንደሚመዘንለት።
3. የሚያስተምር ሰው ምሳሌን እያጠቀሰ ቢያስተምር ጥሩ እንደሆነ።


YOUTUBE.COM|BY ABUADNAN ABUMERIEM


ዝግጅት ፦
በዓብዱልሰመድ መሓመድኑር አሕመድ