Thursday, April 2, 2015

አርቴፊሻል ጥፍር ማስተከል እንዴት ይታያል?



አርቴፊሻል ጥፍር ማስተከል እንዴት ይታያል?

ሰው ሰራሽ ጥፍር ለማስተከል ምክኒያት ሊሆን የሚችለው ከሁለት አንዱ ነው!

1) የተነቀለ ጥፍርን ለመተካት ሊሆን ይችላል፤ ይህ እንደ ህክምና ይታያል። ክልክልም አይሆንም። ለዚህም መረጃ የሚሆነን ቲርሚዚይ የዘገቡትና አልባኒም ሰሂህ ያሉት የዓርፈጃህ ኢብኑል አስዓድ ሀዲስ ነው። በጃሂሊያ ዘመን የተቆረጠ አፍንጫውን የተካበት ብር (silver) ስለበሰበሰ በወርቅ እንዲተካው መልእክተኛው እንደፈቀዱለት ተናግሯል። ይህ የሚያሳየው በዚህ መልክ ጉዳት የደረሰበትን አካል መተካት ችግር እንደሌለው ነው።


እዚህ ላይ ልናጤነው የሚገባው፤
ሀ) ጥፍሩ ረጅም መሆን የለበትም
ለ) ውሀ ከስር ወዳለው የሰውነት ክፍል ይደርስ ዘንድ ለውዱእና ለትጥበት በቀላሉ የሚነሳ አይነት መምረጥ ያስፈልጋል። በጣም የሚያስቸግር ከሆነ ግን ችግር አይኖረውም።

2) ለውበት ጥፍርን መተካት፤
ይህ አይፈቀድም! የዚህም ዋነኛ ምክኒያቱ የአላህን አፈጣጠር መቀየር መሆኑ ነው። እንደዚሁ ሌላ ሰዎች ተፈጥሯዊ ጥፍር እንዲመስላቸው ስለሚያደርግ መሸንገል ነው።

አርቲፊሻል ጥፍር ስለማስረከል በሳውዲ ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴ ተጠይቆ እንደመለሰው፤

" لا يجوز استخدام الأظافر قال علماء اللجنة الدائمة : " لا يجوز استخدام الأظافر الصناعية...؛ لما فيها من الضرر على محالها من الجسم ، ولما فيها -أيضا- من الغش والخداع وتغيير خلق الله ، وبالله التوفيق " انتهى من " فتاوى اللجنة الدائمة ( 17/ 133 ) .

«አርቲፊሻል ጥፍር መጠቀም አይቻልም! ምክኒያቱም፤የሚተከልበት የሰውነት አካል ላይ ጉዳት ያደርሳል! ከዚህም ባሻገር ሰዎችን መሸንገልና ማታለል ነው፤ እንደዚሁ የአላህንም ፍጥረት መቀየር ነው።» በሳውዲ ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴ 17/133

ከ www.facebook.com/tenbihat የተወሰደ።

Sunday, March 15, 2015

6ኛ ሓዲስ






الحديث السادس

الحرام والحلال وفضل الإجتناب الشبهات

عَنْ أَبِي عَبْدِ اللَّهِ النُّعْمَانِ بْنِ بَشِيرٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا، قَالَ: سَمِعْت رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ: "إنَّ الْحَلَالَ بَيِّنٌ، وَإِنَّ الْحَرَامَ بَيِّنٌ، وَبَيْنَهُمَا أُمُورٌ مُشْتَبِهَاتٌ لَا يَعْلَمُهُنَّ كَثِيرٌ مِنْ النَّاسِ، فَمَنْ اتَّقَى الشُّبُهَاتِ فَقْد اسْتَبْرَأَ لِدِينِهِ وَعِرْضِهِ، وَمَنْ وَقَعَ فِي الشُّبُهَاتِ وَقَعَ فِي الْحَرَامِ، كَالرَّاعِي يَرْعَى حَوْلَ الْحِمَى يُوشِكُ أَنْ يَرْتَعَ فِيهِ، أَلَا وَإِنَّ لِكُلِّ مَلِكٍ حِمًى، أَلَّا وَإِنَّ حِمَى اللَّهِ مَحَارِمُهُ، أَلَّا وَإِنَّ فِي الْجَسَدِ مُضْغَةً إذَا صَلَحَتْ صَلَحَ الْجَسَدُ كُلُّهُ، وَإذَا فَسَدَتْ فَسَدَ الْجَسَدُ كُلُّهُ، أَلَا وَهِيَ الْقَلْبُ".
رَوَاهُ الْبُخَارِيُّ [رقم:52]، وَمُسْلِمٌ [رقم:1599].


6ኛ ሓዲስ

የሓዲሱ ትርጉም

ሓላል፣ ሓራም፣ እና ተመሳሳይ ነገሮች

ኑዕማን ኢብኑ በሺር የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋሎህ አለ። የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلمእንዲህ አሉ። “ ሓላል(የተፈቀደ) ነገር ሁሉ ግልጽ ነው። ሃራምም(የተከለከለም) ነገር ግልጽ ነው። በመካከላቸው ደግሞ ብዙ ሰው የማያውቃቸው ተመሳሳይ ነገሮች አሉ።ከነዚህ ተመሳሳይ ነገሮች ራሱን የጠበቀ በርግጥም ዲኑንና (ሃይማኖቱንና) ክብሩን ነጻ አውጥቷል። በነዚህ ተመሳሳይ ነገሮች ላይ የወደቀ ሓራም (ክልክል)ላይ በርግጥም ወደቀ። ተመሳሳይ ነገሮች ላይ የሚወድቅ ሰው አምሳያው ልክ እንደ ወሰን ላይ የሚጠብቅ፥ እንስሶቹ ወሰን አልፈው የሰው እርሻን ሊበሉ እንደቀረቡበት እረኛ ነው። በርግጥም ሁሉም ንጉስ ወሰን አለው፥ የአላህ ወሰን ደግሞ እርም ያደረጋቸው ነገሮች ናቸው። በርግጥም ሰውነት ውስጥ ቁራጭ ስጋ አለች። እሷ ካማረች(ከተስተካከለች) ሰውነት ሁሉ ያምራል(ይስተካከላል)፥ እሷ ደግሞ ከተበላሸች ሰውነት ሁሉ ይበላሻል። ያች ቁራጭ ስጋም ልብ ናት።”
ሓዲሱን ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

ከስድስተኛው ሓዲስ የምንወስዳቸው ትምህርቶች

1. ሓላል ሁሉ ግልጽ እንደሆነ፥ ሓራም ሁሉ ግልጽ እንደሆነ። በመካከላቸው ግን ተመሳሳይ ነገሮች እንዳሉ፥ እነዚህን ተመሳሳይ ነገሮች ደግሞ ጥቂት ሰው ብቻ እንደሚያውቃቸው።
2. አንድ ነገር ሓላል ነው ወይስ ሓራም ብለን ከተጠራጠርን መራቅ እንዳለብን።
3. ተመሳሳይ ነገሮች የሚሰራ ወደ ግልጽ ሓራም ለመውደቅ ቅርብ እንደሆነ።
4. በምሳሌኣዊ አነጋገር ማስረዳት እንደሚቻል።
5. ነብዩ መሓመድ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ሱሓቦችን በደንብ እያብራሩ እንዳስተማሩ።
6. ሰው ጥሩና መጥፎ የሚሆነው ዋናው በልቡ እንደሆነ።
7. የሰው ልጅ ውጩ መበላሸት ውስጡ የመበላሸቱ አመላካች እንደሆነ።


Thursday, February 26, 2015

በሒጃብሽ ላይ ፅናት ይኑርሽ!



www.facebook.com/tenbihat የተወሰደ።

በሒጃብሽ ላይ ፅናት ይኑርሽ!

﴿يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ قُل لِّأَزْوَاجِكَ وَبَنَاتِكَ وَنِسَاءِ الْمُؤْمِنِينَ يُدْنِينَ عَلَيْهِنَّ مِن جَلَابِيبِهِنَّ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَن يُعْرَفْنَ فَلَا يُؤْذَيْنَ ۗ وَكَانَ اللَّـهُ غَفُورًا رَّحِيمًا﴾
الأحزاب 59


«አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ
እንዲለቁ ንገራቸው፡፡ ይህ (በጨዋነታቸው) እንዲታወቁና 
(በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመኾን በጣም የቀረበ ነው፡፡ 
አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡» 
አል አህዛብ 59

ጅልባብ ማለት ሰውነትን በሙሉ ከላይ ጀምሮ የሚሸፍን ሰፊ የሆነ የልብስ አይነት ነው። አላህ ነብዩን ለሚስቶቻቸው ለልጆቻቸው እንዲሁም ለምእመናት በሙላ ጅልባቦቻቸውን በላያቸው ላይ በመልቀቅ ፊቶቻቸውንና ደረቶቻቸውን ይሸፍኑ ዘንድ እንዲነግሩ አዟቸዋል።

ሴት ልጅ ፊቷን ባእድ ከሆኑና ሙህርሟ ካልሆኑ ወንዶች የመሸፈን ግዴታ እንዳለባት ከቁርንአንና ከሱና የሆኑ ማስረጃዎች አመላክተዋል። አንዲት ሴት ሰውነቷን ከራሷ ጀምሮ እስከ እግሮቿ ድረስ እንድትሸፍን እንዲሁም በእግሯ ላይ ያደረገችው ጌጥ ድምፅ እንዳያሰማ በእግሯ መሬቱን እንዳትመታ ከታዘዘችና በዚህ መልኩ መሸፈን በሷ ላይ ግድ ከሆነ ፊቷን መሸፈኗ ደግሞ በበለጠ ሁኔታ ግድ እንደሚሆንባት ያስተዋይ አእምሮ ባለቤት አይጠራጠርም።

ይህም የሚሆነው ፊቷን በመክፈቷ ሊከሰት የሚችለው ፊትና ጸጉሯን በመክፈቷ ሊከሰት ከሚችለው ፊትና ወይንም የእግር ጥፍሮቿን በመክፈቷ ሊከሰት ከሚችለው ፊትና እጅግ የከበደ በመሆኑ ነው። የአንድ ሙእሚን ሰው አእምሮ የዚህን ሸሪአዊ ህግ ጥበብና ሚስጥር በሚያስተነትን ጊዜ ሴት ልጅ ጸጉሯን አንገቷን ክንዶቿን ባቷንና እግሮቿን ሸፍና እጆቿንና በውበት የተሞላ ፊቷን ከፍታ ትሄድ ዘንድ መፍቀዱ በፍጹም ከሸሪአዊው ጥበብ ጋር ተቃራኒ መሆኑን ያስተውላል።

በአሁን ዘመን ላይ ያለውን የሰዎችን ፊትን በመሸፈን ላይ ያለውን ቸልተኝነት በአንዳንድ ሙስሊም ሃገሮች ሴት ልጅ ከፊቷ ውጪ ያሉትን እንደ ራስ አንገት ደረትና ክንዶቿን ግልታ በየገበያው ላይ በግድ የለሽነት እንድትሄድ እንዳደረገት ያስተዋለ ሰው ሴት ልጅ ፊቷን እንድትሸፍን ያዘዛትን ሸሪአዊ ጥበብ ቁርጠኛ የሆነ ማወቅን ያውቃል።

አንቺ ሙስሊም ሴት ሆይ! አላህን በመፍራት ያንን ከፊትና የጸዳውንና ዋጅብ የሆነውን ከባለቤትና ሙህሪም ከሚሆኑ ወንዶች በስተቀር መላ ሰውነትን የሚሸፍነውን ሸሪአዊ ሂጃብ ልትለብሺ ይገባል። ሴት ልጅ ፊቷንና አንዳንድ የሰውነት ክፍሎቿን ባእድ ለሆኑ ወንዶች መግለጿን ባስተዋልን ጊዜ ብጣም ብዙ የሆኑ ጥፋቶችም ሰብስቦ ይዞ እናገኛለን።

በዚህ ነገር ውስጥ ጥቅም ሊኖር ይችላል ብንል እንኳን ይህ ጥቅም እጅግ በጣም ትንሽ በመሆኑ ከጥፋቶች ውስጥ ተከልሎ ሊታይ አይችልም።

አንዳንዶች የኒቃብን ሸሪዓዊ ብይን አስመልክቶ፤
"ዋጂብ ነው ወይስ መልበሱ በላጭ የሆነ (አፍደል)? " በሚል ጉንጭ አልፋ ክርክር ሴቶችን በማዋከብ ከኒቃብ ያርቃሉ።

ያንቺ አቋም የሚሆነው፤
☞ ዋጂብ ከሆነ መልበስ ግዴታዬን መወጣት ነው!
☞ ዋጂብ ያልሆነ ትርፍ ስራ ከሆነ ከማንም በላይ ወንጀሌን የሚያስምርና ደረጃዬን ከፍ የሚያደርግ መልካም ስራ ያስፈልገኛል የሚል ይሁን።

አላህ ሆይ!

ትክክለኛውን ኢስላማዊ ሂጃብ በመተግበር ላይ ፅናቱን ለግሰኝ!!

www.facebook.com/tenbihat የተወሰደ።

Sunday, February 8, 2015

የጀናዛ ሰላት አሰጋገድ።



የጀናዛ ሰላት አሰጋገድ

አራት ጊዜ ተክቢራ ይደረጋል፤

☞ ከመጀመሪያ ተክቢራ በመቀጠል አል ፋቲሀ (የመክፈቻው ምዕራፍ) ይነበባል። ከዚህም በተጨማሪ አጠር ያለ የቁርአን ምዕራፍ ወይም አንድ ወይም ሁለት አንቀፅ ቢያነብ ጥሩ ነው። ይህንን በማስመልከት ከአብደላህ ኢብን አባስ የተዘገበ ትክክለኛ ሀዲስ ስላለ ነው።


☞ ከዚያም ለሁለተኛ ጊዜ ተክቢራ ይደረጋል፤
ከተሸሁድ ቀጥሎ እንዳለው በነብዩ ላይ ሰለዋት ያወርዳል። ከዚያም በሶስተኛው ተክቢራ ከተደረገ በኃላ እንዲህ ይላል

(اللهم اغفر لِحينا وميتِنا، وشاهدنا وغائبنا، وصغيرنا وكبيرنا، وذَكَرِنا وأنثانَا، اللهم من أحيَيتَهُ منا فأحيه على الإسلام، ومن توفيته منا فَتَوَفهُ على الإيمان، اللهَم اغفر له، وارحمه، وعافه، واعف عنه، وأكرِم نُزُلَه، وَوَسع مُدخَلَه، واغسله بالماء والثلج وِالبرد، ونقه من الخطايا كما ينقى الثوب الأبيض من الدَنس، وأبدلهُ دارا خيرا من داره، وأهلا خيرا من أهله، وأدخله الجنة، وأعذه من عذاب القبر، وعذاب النار، وافسح له في قبره، ونور له فيه، اللهم لا تَحرمنَا أجره ولا تُضِلنا بعده)

(አላሁመ ኢግፊር ሊሐይና ወመይቲና ወሻሂድና ወጋኢቢና ወሰጊሪና ወከቢሪና ወዘከሪና ወኡንሳና አላሁመ መን አህየይተሁ ሚና ፈአህይሂ አለል ኢስላም ወመን ተወፈይተሁ ሚና ፈተወፈሁ አለል ኢማን አላሁመ ኢግፊር ለሁ ወግሲልሁ ቢልማኢ ወሰልጂ ወልበረዲ ወነቂሂ ሚነል ዙኑቢ ወል ኸጣያ ከማ ዩነቀሰውቡል አብየዲ ሚነደነሲ ወአብዲልሁ ዳረን ኸይረን ሚን ዳሪህ ወአህለን ኸይረን ሚን አህሊህ ወአድኺሉሁል ጀነተ ወአዒዙሁ ሚን ዓዛቢል ቀብሪ ወዓዛቢ ናር ወፍሰህ ለሁ ፊ ቀብሪሂ ወናዊርለሁ ፊህ አላሁመ ላተህሪምና አጅረሁ ወላቱዲለና ባዕደሁ።)

ትርጉሙም: “አላህ ሆይ በህይወት ያሉትንም፣ የሞቱትንም፣ በቅርብ ያለውንም ሩቅ ያለውንም፣ ትልልቆችንም፣ ትንንሾችንም፣ ወንዶችንም ፣ ሴቶችንም ማርልን። አላህ ሆይ ከመካከላችን የምትገለውን በእምነት ላይ እንዲሞት አድርገው። አላህ ሆይ ምህረት አድርግለት፣ እዘንለትም፣ ከእሳት ጠብቀው፣ ይቅርም በለው፣ መስተንግዶውን አሳምርለት፣ መግቢያውንም አስፋለት፣ አጢአቱንም በውሃ፣ በበረዶና በቀዝቃዛ ውሃ እጠብለት፣ ነጭ ልበስ ከቆሻሻ እንደሚፀዳው የእርሱንም ወንጀል አፅዳለት፣ ከቤቱ የተሻለ ቤት ከሚስቱ የተሻለ ሚስት ቀይርለት። ወደ ገነት አስገባው፣ ከቀብር ውስጥ ቅጣትና ከእሳትም ቅጣት ጠብቀው ቀብሩንም አስፋለት፣ አብራለት። አላህ ሆይ ምንዳውን አትንፈገን ከእርሱም በኃላ እጣችንን ጥመት አታድርግብን።”
ማለት ነው።

☞ ከአራተኛው ተክቢራ በኃላ በቀኝ ጐኑ ብቻ “አሰላሙአለይኩም” በማለት ያጠናቅቃል።

ተክቢራ በሚደረግበት ጊዜ እጅን ማንሳት ይወደዳል።
√ ሴት ከሆነች ዱዓው ላይ እንዲህ ይባላል፤
(اللهم اغفر لها . . ) (አላሁመ እግፊርለሃ) 
√ ሁለት ከሆኑ ደግሞ (اللهم اغفر لهما . . . ) (አላሁመ እግፊር ለሁማ) 
√ ከሁለት በላይ ከሆኑ ደግሞ (اللهم اغفر لهم . . ) (አላሁመ እግፊር ለሁም) ይባላል። 
√ ሟቹ ህፃን ከሆነ ለእርሱ ምህረትን በዱዓው ውስጥ ከመለመን ይልቅ እንዲህ ይባላል።

(اللهم اجعله فرطا وذُخْرَا لوالديه، وشفيعاَ مُجَابا، اللهم ثقل به موازينهما، وأعظم به أجورهما، وألحقه بصالح سلف المؤمنين، واجعله في كفالة إبراهيم عليه الصلاة والسلام، وَقِهِ برحمتك عذاب الجحيم)

(አላሁመ ኢጅዓሉሁ ፈረጠን ወዙኽረን ሊዋሊደይሂ ፤ ወሸፊዓን ሙጃበን አሏሁመ ሰቂል ቢሂ መዋዚነሁማ፤ ወአዕዚም ቢሂ ኡጁረሁማ፤ ወአልሂቁሁ ቢሷሊሂ ሰለፊልሙእሚኒን፤ ወጅዓልሁ ፊ ከፋለቲ ኢብራሂመ አለይሂ ወሰላቱ ወሰላም ወቂሂ ቢራህመቲከ አዛበል ጀሂም)

√ ትርጉሙም “አላህ ሆይ በወላጆቹ (በወዲያኛው ህይወት) ቀደሞ ሄዶ የሚያመቻች፣ ለችግር ቀን አለኝታ፣ ተሰሚነት ያለው አማላጅ አድርግላቸው፣ አላህ ሆይ የመልካም ስራቸው ሚዛን ማክበጃና የምንዳቸው ማብዣ አድርገው፣ ከደጋግ ምእመናን ጋርም አስጠጋው ከነብዩ ኢብራሂም u እንክብካቤ ስር አድርገው፣ በችሮታህም ከጀሐነም እሳት ጠብቀው።”

☞ ኢማሙ በሟች ላይ ለመስገድ ሲቆም ወንድ ከሆነ በጭንቅላቱ አቅጣጫ ሴት ከሆነች በሰውነቷ መሀል አቅጣጫ መቆሙ ሱና ይሆናል።

☞ አስክሬኑ ወንድና ሴት ከሆኑ ወንዱ ወደ ኢማሙ በኩል ሴቷ ወደ ቂብላ በኩል ይደረጋሉ ።

ከ www.fb.com/easyfiqh የተወሰደ።


Friday, January 23, 2015

Saturday, January 10, 2015

الحديث الخامس


الحديث الخامس
حرمة الإبتداع في الدين
عَنْ أُمِّ الْمُؤْمِنِينَ أُمِّ عَبْدِ اللَّهِ عَائِشَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهَا، قَالَتْ: قَالَ: رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم "مَنْ أَحْدَثَ فِي أَمْرِنَا هَذَا مَا لَيْسَ مِنْهُ فَهُوَ رَدٌّ". رَوَاهُ الْبُخَارِيُّ [رقم:2697]، وَمُسْلِمٌ [رقم:1718].
وَفِي رِوَايَةٍ لِمُسْلِمٍ:"مَنْ عَمِلَ عَمَلًا لَيْسَ عَلَيْهِ أَمْرُنَا فَهُوَ رَدٌّ" .

5ኛ  ሓዲስ
የሓዲሱ ትርጉም
በዲን አዲስ ነገር ማምጣት የተከለከለ እንደሆነ።
የሙእሚኖች እናት የሆነችው ዓኢሻ እንዲህ አለች። የአላህ መልእክተኛ  صلى الله عليه وسلم  እንዲህ አሉ። “ በዚህ ዲናችን ከሱ ያልሆነን አዲስ ነገር የፈጠረ ስራው ተቀባይነት የለውም ወደራሱ ተመላሽ ይሆናል።”
ሓዲሱን ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

ከአምስተኛው ሓዲስ የምንወስዳቸው ትምህርቶች
1.      በዲን አዲስ ነገር የተሰራ ሁሉ ተቀባይነት እንደሌለው። ሰውየው ጥሩ ንያ ቢኖረውም።
2.     በዲን የታዘዝነውን ስራ ባልታዘዝነው መልኩ መስራት የተከለከለ እንደሆነ።


Friday, December 5, 2014

📌 የሰጋጅ መከለያ (ሱትራ)📌




📌 የሰጋጅ መከለያ (ሱትራ)📌

የሶላት መከለያ ሰጋጅ በራሱና ከፊቱ አቋርጦ በሚያልፍ ሰው መካከል
የሚያደርገው መከለያ ነገር ነው፡፡

√ የሰጋጅ መከለያ ሱትራ የተደነገገ ስለመሆኑ

በጉዞ ላይም ሆነ ከጉዞ ውጭ፣በግዴታም ሆነ በሱንና ሶላት፣በመስጊድም ሆነ በሌላ ቦታ የሰጋጅ መከለያን (ሱትራ) ማድረግ የተደነገገ ነው፡፡

📋 ነቢዩ ﷺ :- ‹‹አንዳችሁ በሚሰግድበት ጊዜ ወደ መከለያ (ሱትራ) ይስገድ፤ወደ መከለያውም ቀረብ ይበል፡፡›› ብለዋልና፡፡
(በአቡ ዳዉድ የተዘገበ)

📋 አል ኢማም አህመድ በዘገቡት ሀዲስ ወህብ (ረዐ) ፡- ‹‹ነቢዩ ﷺ ሚና ላይ ሲያሰግዱን አንካሴ ከፊትለፊታቸው ተከሉና ሁለት ረክዓ መርተው አሰገዱን፡፡» ብለዋል።

√ የሰጋጅ መከለያን የሚመለከት ብያኔ

መከለያ (ሱትራ) ማድረግ ለሰጋጅ ዋጅብ ነው፡፡ ነቢዩ ﷺ ኢማምም ሆነ ለብቻው የሚሰግድ ሰው መከለያ ነገር ከፊት ለፊቱ እንዲደርግ አዘው አበረታተዋል፡፡ በመሆኑም አንድ ሙስሊም በሚሰግድበት ጊዜ ከፊትለፊቱ መከለያ ነገር አድርጎ በርሱና በመከለያው መካከል ሰው አቋርጦ እንዳያልፍ መከልከል ይገበዋል፡፡

📋 ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «ወደ ሱትራ እንጂ አትስገድ፤ ከፊትለፊትህ እንዲያልፍ ለማንም አትፍቀድ፤ እምቢ ካለህ ከሱ ጋር ሸይጣን አለውና ታገለው።»
ኢብኑ ኹዘይማ ዘግበውታል አልባኒም ሰሂህ ብለውታል።

√ የሰጋጅ መከለያ ያዘለው ጥበብ

መከለያ (ሱትራ) ለሰጋጅ የተደነገገው በርካታ ጥበቦችን አካትቶ ሲሆን ከዚህ ውስጥ፡-

1- ትኩረቱንና ተመስጦውን የሚሻማ በመሆኑ በሚሰግድ ፊት ማቋረጥን ለመከልከል፡፡

2- ሰጋጁ ሙሉ ሃሳቡንና ትኩረቱን በሶላቱ ላይ እንዲያደርግና በሌላ ጣልቃ ገብ እንዳይወሰወስ ለማድረግ፡፡

3- በሴት በውሻ ወይም በአህያ አቋርጦ ማለፍ ሶላት እንዳይቋረጥ ጥንቃቄ ለማድረግ፡፡

📋 ከአቡ ዘር (ረዐ) በተላለፈው መሰረት የአላህ መልእክተኛ ﷺ ፡- ‹‹አንዳችሁ ለመስገድ በሚነሳበት ጊዜ፤ የኮርቻ የኋላ መደገፊያ ያህል ነገር ከፊትለፊቱ ካለ መከለያ ይሆነዋል፤ የኮርቻ የኋላ መደገፊያ ያህል ነገር ከፊትለፊቱ ከሌለ ግን ሶላቱን አህያ፣ሴትና ጥቁር ውሻ ያቋርጥበታል፡፡›› አሉ ሲሉኝ፣ አቡ ዘር ሆይ! ጥቁር ዉሻን ከቀይ ወይም ከብጫ ዉሻ ምን ለየው? አልኳቸውና የወንድሜ ልጅ! አንተ አንደጠየከኝ ሁሉ እኔም የአላህ መልእክተኛን ﷺ ጠይቄ ፡-‹‹ጥቁር ዉሻ ሰይጣን ነው፡፡›› አሉ ብለውኛል፡፡ 
(ሙስሊም ዘግበውታል)

√ ሱትራን ከሚመለከቱ ድንጋጌዎች በከፊል

1- መከለያ ማድረግ ለኢማም ወይም ለብቻው ለሚሰግድም ይሆናል፡፡ ተከትሎ ለሚሰግድ ሰው ኢማሙ ለርሱ መከለያው ነው፡፡

📋 ኢብን ዐባስ (ረዐ) ባስተላለፉት መሰረት ፡- ‹‹የአላህ መልእክተኛ ﷺ በሚና ሰዎችን በማሰገድ ላይ እያሉ፣ ያኔ ለአቅመ አዳም የደረስኩ ነበርኩ፤ አንድ እንስት አህያ ላይ የተቀመጠ ሰው አግኝቼ በአንዳንዶቹ የሶላት ሰፎች ፊት ለፊት አቋርጬ አለፍኩና ከአህያዪቱ ወርጄ እንድ ግጥ ለቀቅኳት፤ ከዚያ ወደ ሶላት ሰፉ ገባሁ፤ ማንም ሰውም ድርጊቴን አልተቃወመም፡፡›› ብለዋል፡፡

ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ኢማሙ ነወዊ፤ ይህ ሀዲስ የኢማሙ ሱትራ የሰገሰጆች ሱትራ መሆን እንደሚችል ያሳያል ብለዋል።

የኢማሙ ሱትራ የሰገሰጆችም ሱትራ ስለሆነ በመካከል ሰው ማለፉ ሳይሆን የሚከለከለው በኢማሙ ፊት ማለፉ ነው።

ኢብኑ አብድልበር አልኢስቲዝካር በሚለው መፅሀፋቸው ላይ ይህንን ሲያስረዱ፤ የኢማሙ ሱትራ የሰገሰጆችም ሱትራ እንደሆነ ከሚያስረዱት መካከል ሂሻም ኢብንል ጋዚ ከናፍእ ናፍእ ደግሞ ከኢብኑ ኡመር የዘገቡት ሀዲስ ነው።

ኢብኑ ኡመር እንዲህ ብለዋል፤ 
የአላህ መልእክተኛ ዙህርን ወይም አስርን እያሰገዱ ሳለ እንስሳ ከፊታቸው ልታልፍ ስትሞክር ሊመልሷት ሞከሩ፤ ማለፊያውን ሲያጠቡባትም ትኬሻቸው ግድግዳውን እንደነካ አይቻለው። ከዛም ከበስተጀርባቸው አለፈች።»

ይህም ከበስተጀርባ ስላለፈች ነው።

«የኢማሙ ሱትራ የተከታዮች ሱትራ ነው» የሚለውንም ከኢብኑ ኡመር አብዱረዛቅ ዘንድ ተዘግቧል።

2- በሰጋጅ ሰው ፊት አቋርጦ ማለፍ አይፈቀድም፡፡ ያለፈ ሰው ሀጢያተኛ ይሆናል፡፡

📋 ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል ፡- ‹‹በሚሰግድ ሰው ፊት አቋርጦ የሚያልፍ ሰው ምን (ያህል ከባድ ኃጢአት) እንዳለበት ቢያውቅ ኖሮ አቋርጦት ከሚያልፍ አርባ መቆም የተሻለ በሆነለት ነበር፡፡›› አቡ ነድር - ዘጋቢው - አርባ ቀን ወር ወይም ዓመት ይበሉ አላውቅም ብለዋል፡፡
በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ

አቋርጦ ማለፉ ከመከለያ ወዲያ ወይም ሰጋጁ መከለያ ካላደረገ ከሱጁዱ ቦታ ራቅ ብሎ ከሆነ ግን ይፈቀዳል፡፡

3- ሰጋጁ አቋርጦት የሚያልፈውን ሰው መከልከል አለበት፡፡

📋 አቡ ሰዒድ አልኹድሪ (ረዐ)
ነቢዩﷺ ፡- ‹‹አንዳችሁ ከሰዎች የሚከልለውን ነገር ከፊቱ አድርጎ ከሰገደና ሌላ ሰው ከፊትለፊቱ አቋርጦ ማለፍ ቢፈልግ ይገፍትረው፣እምቢ ካለም ይፋለመው፤ሰይጣን እንጂ ሌላ አይደለምና፡፡›› ሲሉ ሰምቻለሁ ብለዋል፡፡ ይህንንም በቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

4- ከእውቀት ባለቤት ዑለማእ መካከል ከፊሎቹ፤ «አስቸጋሪ ሁኔታን ማስወገድ» ከሚል አጠቃላይ መርሕ መሰረት በመካው የተከበረ መስጊድ ሰጋጅ ፊት ማቋረጥን ፈቅደዋል፡፡ ይህም በተከበረው መስጊድ ውስጥ ሰጋጅ ፊት አቋርጦ ማለፍን መከልከል በአብዛኛው ከባድ ችግር የሚፈጥር በመሆኑ ነው፡፡

5- ወደ ግድግዳ ወይም ከመስጊድ ምሶሶዎች መካከል ወይም ከመደርደሪያዎች ወደ አንዱ በመጠጋት ወይም እንደ ዱላ ያለ ነገር በማኖር መከለያ ማድረግ ይቻላል፡፡

6- በሰጋጁና በመከለያው መካከል ያለው ርቀት በአንድ ፍየል መተላፊያ በሚበቃ ያህል ይሰላል፡፡

📋 ሰህል እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹በአላህ መልእክተኛ ﷺ መስገጃና በግድግዳው መካከል የፍል መተላለፊያ ያህል ርቀት ነበር፡፡›› 
በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ

ማሳሰቢያ፦ 
የሴት ሶላትን መቁረጥ ከላይ በሰፈረውና ‹‹ሶላቱን...ያቋርጥበታል›› በሚለው ሐዲስ ውስጥ ሴትን ከአህያና ከጥቁር ዉሻ ጋር የሚያነጻጽር ነገር የለበትም፡፡ 
የሦስቱ በአንድ ዐረፍተ ነገር አገባብ ውስጥ መገኘት፣ የሦስቱ ማለፍ ሶላት እንዲቋረጥ የሚያደርግበት ምክንያት አንድ ዓይነት ነው ማለት አይደለም፡፡
ማለትም ጥቁር ዉሻ ሶላት የሚቆርጥበት ምክንያት በአህያ ወይም በሴት ሁኔታ ሶላቱ ከሚቋረጥበት ምክንያት ጋር አንድ ነው ማለት አይደለም፡፡ ስለዚህም በሐዲሱ ውስጥ እንደ ተጠቀሰው ጥቁር ዉሻ ሰይጣን መሆኑ አህያ ወይም ሴት ሰይጣን ናቸው ማለት አይደለም፡፡ ሦስቱ በአንድ አገባብ ቢቀርቡም የተለያየ ምክንያት አላቸው፡፡ የዉሻው ምክያት ከተቀሩት ሁለቱ ተለይቶ በሐዲሱ የተጠቀሰ መሆኑ የተለያዩ መሆናቸውን እንጂ ተመሳሳይ መሆናቸውን አያመለክትም።

የሴቷ ሶላት መቁረጥ ከሰጋጁ ቀረብ ብላ አጠገቡ ማለፏ የወንዱን ስሜት ሊቀሰቅስና በሶላቱ ላይ ያለውን ተመስጦና ትኩረቱን ሊበታትንበት ይችል ይሆናል፡፡ ስለዚህም ጠቅለል ባለ መልኩ ሲታይ ከሌላው ወንድ ተላላፊ ይበልጥ ሴት ተላላፊ ትኩረቱን ትስባለች፡፡ ለዚህ ነው -ይበልጥ የሚያውቀው አላህ ነው - በሸሪዓው የሶላትን ተመስጦና ኹሹዕ ለመጠበቅ ሲባል የሴት ልጅን በሰጋጅ ፊት ማለፍ ሶላትን ከሚቆርጡት አንዱ ያደረጋት፡፡

🔚 አይሰስቱ...
ቢያንስ ለ3 ሰው ሼር ያድርጉ!

Source: amharicfiqh.com ከማስተካከያና ጭማሪዎች ጋር የቀረበ።

📹 የሰጋጅ መከለያ (ሱትራ) 

ዓላማችን ኢስላማዊ እውቀትን ማዳረስ ነው::


SHARE