Tuesday, June 10, 2014

(New App) ዝክረ ረመዳን



(New App) ዝክረ ረመዳን


― ― ― ― ― ― ― ― ―

ምስጋና ለአለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ነው። የአላህ ሰላምና እዝነት በነብያችን ሙሐመድ ﷺ እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው ሁሉ ላይ ይሁን።

ረመዳንን መፃም ከኢስላም መሰረቶች አንዱ ነው። ማንኛውም ኢባዳ ስኬታማ ያደርገን ዘንድ እውቀትን መሰረት ያደረገ ሊሆን ይገባዋል። 

በቅርቡ የረመዳንን ህግጋት የየዘ አዲስ App እንደምንለቅ ቃል በገባነው መሰረት የአላህ ፍቃድ ሆኖ እነሆ ቀርቦላችኋል። 

«ዝክረ ረመዳን» በሚል ርእስ የተዘጋጀው ይህ የሞባይል አፕሊኬሽን App ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ይታመናል። እጅግ ብዙ ጠቃሚ መረጃዎች ተካተውበታል።

በሚገባ በመጠቀም እና ለሌሎችም በማስተላለፍ ሀላፊነትዎን ይወጡ። 

ይህንን App በማዘጋጀት ሂደት አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሁሉ አላህ መልካም ምንዳን እንዲከፍላቸው እንለምነዋለን። 

በአላህ ፈቃድ እና እገዛ በቅርቡ፤ የኦሮምኛ እና የትግርኛ ቋንቋዎችን በማከል update ይኖረናል። 

ሸእባን 7/ 1435

ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር

SHARE

Friday, June 6, 2014

የአዛንና ኢቃም ትርጉሞችና ሸሪዓዊ ድንጋጌዎቻቸው




የአዛንና ኢቃም ትርጉሞችና ሸሪዓዊ ድንጋጌዎቻቸው

ሀ. የአዛንና የኢቃም ትርጉም፦

አዛን ማለት የዓረብኛ ቋንቋ ትርጉሙ ማሳወቅ ማለት ነው፡፡ 
አላህ እንዲህ ብሏል፡-
“ይህ) ከአላህና ከመልክተኛው በታላቁ ሐጅ ቀን የወጣ ወደ ሰዎች የሚደርስ ማስታወቂያ ነው”(9:3)

ሸሪዓዊ ትርጉሙ፦ በተወሰኑ ዚክሮች የሰላት ወቅት መድረሱን ማሳወቅ ማለት ነው፡፡
ኢቃማ ማለት ደግሞ የዓረብኛ ቋንቋ ትርጉሙ የተቀመጠን ማስነሳት ማለት ሲሆን ሸሪዓዊ ትርጉሙ በሚታወቁ ዚክሮች ለሰላት እንዲቆም የሚደረግ ጥሪ ማለት ነው፡፡

ለ. ሸሪዓዊ ድንጋጌያቸው፦
አዛንና ኢቃም ለአምስት ሰላቶች ወንዶች ላይ “فرض كفاية” (በተወሰኑ ሰዎች ላይ ብቻ ግዴታ) የሆነ ሲሆን በቂ ሰው ከፈፀመው ግዴታነቱ ከሁሉም ይነሳል፡፡

ሁለተኛ

ትክክለኛ እንዲሆኑ መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
1. ሙስሊም መሆን፡- ካፊር ቢፈፅማቸው ትክክለኛ አይሆኑም
2. አእምሮ ጤናማ መሆን፡- ልክ እንደሌሎች አምልኮቶች እብድ በስካር ላይ ያለና ህፃን ቢፈፅማቸው ትክክል አይሆኑም፡፡
3. ወንድ መሆን፡- ሴት ድምጿ ፈታኝ በመሆኑ አዛን ማድረግ የለባትም፡፡ እንዲሁም ፍናፍንት ከሆነ ወንድነቱ ስለማይታወቅ አዛንና ኢቃም ማድረግ የለበትም፡፡
4. አዛኑን በሰላት ወቅት ማድረግ፡- ለሱብሂና ለጁምዓ የመጀመሪያዎች አዛን ካልሆነ በቀር የሰላት ወቅት ሳይደርስ አዛን ማድረግ አይፈቀድም፡፡ ኢቃም የሚደረገው ደግሞ ሰላት ውስጥ ለመግባት ሲፈለግ መሆን አለበት፡፡
5. አዛንና ኢቃም ሲደረግ ቅደም ተከተላቸውን የጠበቀ ተከታታይ የሆኑ ቃላቶች መሆን አለባቸው፡፡ የአደራረጉ ሁኔታ አራተኛው ነጥብ ላይ ይገለፃል፡፡ 
6. አዛንና ኢቃም ሸሪዓው በደነገጋቸው ቃላቶችና በዓረብኛ ቋንቋ መደረግ አለባቸው፡፡


አዛን ትክክለኛ እንዲሆኑ መሟላት ካለባቸው መስፈርቶች አንዱን ጥቀሱ?

ከ 
የተወሰደ ።


Tuesday, June 3, 2014

የሰላት ወቅቶች። የመግሪብ ሰላት ወቅት ፣ የሱብሂ ሰላት ወቅት





የመግሪብ ሰላት ወቅት

የመግሪብ ሰላት ወቅት ፀሐይ ከጠለቀበት ሰዓት ጀምሮ ደንገዝ እስከሚል (ፀሀይ መጥለቂያ ጋር የሚኖረው የሰማይ ቅላት እስከሚሰወር) ሲሆን መግሪብንም በመጀመሪያው ወቅት ላይ መስገድ ሱና ነው፡፡ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል 
“ህዝቦቼ መግሪብን ከዋክብት እስኪጠላለፉ ድረስ ካላዘገዩ በመልካም ላይ ናቸው፡፡” (አህመድ አቡዳውድና ሃኪም ዘግበውታል)
የሐጅ ተግባር ላይ ያለ ሰው ግን የሙዝደሊፋን ሌሊት መግሪብን ወደ ዒሻ አዘግይቶ ከዒሻ ጋር መስገዱ የተወደደ ተግባር ነው፡፡
የዒሻ ሰላት ወቅት

የዒሻ ሰላት ወቅት ደግሞ እስከ እኩለ ለሊት የሚቆይ ሲሆን ዒሻን ግን አስቸጋሪ ካልሆነ አዘግይቶ በመጨረሻው ወቅት መስገድ ይበልጥ የተወደደ ነው፡፡ ከዒሻ በፊት መተኛትና ከዒሻ በኋላ ደግሞ ወሬ ማውራት የተጠላ ነው::
አቡ በርዛህ ባስተላለፉት ሀዲስ 
“ነብዩ ከዒሻ በፊት መተኛትና ከዒሻ በኃላ ማውራት ይጠሉ ነበር::”(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

የሱብሂ ሰላት ወቅት

የሱብሂ ሰላት ወቅት ደግሞ ጐህ ከቀደደ ጀምሮ ፀሐይ እስክትወጣ ድረስ ሲሆን የጐህ መቅደድ እንደተረጋገጠ ወዲያው መስገድ የተወደደ ነው፡፡
እነዚህ ለሰላት የተደነገጉ ወቅቶች በመሆናቸው ማንኛውም ሙስሊም የሰላት ወቅቶችን እየተጠባበቀ ሳያዘገይ በተወሰነላቸው ወቅቶች ሊሰግድ ይገባል፡፡ አላህ ሰላትን የሚያዘገዩን ሰዎች እንዲህ በማለት ዝቶባቸዋል፡-
‹‹ወዮላቸው ለሰጋጆች፡፡ ለእነዚያ እነርሱ ከስግደታቸው ዘንጊዎች ለኾኑት፤ (ሰጋጆች)፡፡›› (አል ማዑን 4-5)
በሌላ አንቀፅም እንዲህ ብሏል፦
‹‹ከእነሱም በኋላ ሶላትን ያጓደሉ (የተዉ) ፍላጎቶችንም የተከተሉ መጥፎ ምትኮች ተተኩ! የገሀነምንም ሸለቆ በእርግጥ ያገኛሉ፡፡›› (መርየም 59)
ሰላቶችን በወቅቶቻቸው መስገድ አላህ ዘንድ በጣም ከሚወደዱና ብልጫ ካላቸው ስራዎች የሚመደብ ነው፡፡ ነብዩ (ﷺ) አላህ ዘንድ በጣም የሚወደድን ስራ ሲጠየቁ 
“ሰላቶችን በወቅቶቻቸው መስገድ” በማለት መልሰዋል:: (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

የዕለቱ ጥያቄ ይሳተፉ
ነብዩ (ﷺ) አላህ ዘንድ በጣም የሚወደድን ስራ ሲጠየቁ የመለሱት ምን በማለት ነው?

ከ www.facebook.com/easyfiqh የተወሰደ።


Sunday, June 1, 2014

ከአርበዒን አን-ነወውያህ 4ኛ ሓዲስ ከከፋ (መጥፎ) መጨረሻ መፍራት


الحديث الرابع

عَنْ أَبِي عَبْدِ الرَّحْمَنِ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ مَسْعُودٍ t قَالَ: حَدَّثَنَا رَسُولُ اللَّهِ r -وَهُوَ الصَّادِقُ الْمَصْدُوقُ-: "إنَّ أَحَدَكُمْ يُجْمَعُ خَلْقُهُ فِي بَطْنِ أُمِّهِ أَرْبَعِينَ يَوْمًا نُطْفَةً، ثُمَّ يَكُونُ عَلَقَةً مِثْلَ ذَلِكَ، ثُمَّ يَكُونُ مُضْغَةً مِثْلَ ذَلِكَ، ثُمَّ يُرْسَلُ إلَيْهِ الْمَلَكُ فَيَنْفُخُ فِيهِ الرُّوحَ، وَيُؤْمَرُ بِأَرْبَعِ كَلِمَاتٍ: بِكَتْبِ رِزْقِهِ، وَأَجَلِهِ، وَعَمَلِهِ، وَشَقِيٍّ أَمْ سَعِيدٍ؛ فَوَاَللَّهِ الَّذِي لَا إلَهَ غَيْرُهُ إنَّ أَحَدَكُمْ لَيَعْمَلُ بِعَمَلِ أَهْلِ الْجَنَّةِ حَتَّى مَا يَكُونُ بَيْنَهُ وَبَيْنَهَا إلَّا ذِرَاعٌ فَيَسْبِقُ عَلَيْهِ الْكِتَابُ فَيَعْمَلُ بِعَمَلِ أَهْلِ النَّارِ فَيَدْخُلُهَا. وَإِنَّ أَحَدَكُمْ لَيَعْمَلُ بِعَمَلِ أَهْلِ النَّارِ حَتَّى مَا يَكُونُ بَيْنَهُ وَبَيْنَهَا إلَّا ذِرَاعٌ فَيَسْبِقُ عَلَيْهِ الْكِتَابُ فَيَعْمَلُ بِعَمَلِ أَهْلِ الْجَنَّةِ فَيَدْخُلُهَا".
رَوَاهُ الْبُخَارِيُّ [رقم:3208]، وَمُسْلِمٌ [رقم:2643].  

4ኛ  ሓዲስ

ከከፋ (መጥፎ) መጨረሻ መፍራት

ከአራተኛው ሓዲስ የምንወስዳቸው ትምህርቶች

1.      የሰው ልጅ ሆድ ውስጥ እያለ ለሱ የተመደበ መላኢካ እንዳለ።
2.     የሰው ልጅ ሁኔታዎች፣ ሲሳዩ፣ ስራው፣ ፍጻሜው፣ ደስተኛ ነው ወይስ የተከፋ የሚለው ሁሉ ገና በናቱ ሆድ ውስጥ እያለ እንደተጻፈ።
3.     በዚች ዓለም የሚከሰተው ክስተት ሁሉ በአላህ የተወሰነ እና ሁሉም ደግሞ ለውሑል መሕፉዝ ላይ የተጻፈነ እንደሆነ።
4.     የሰው ልጅ እስኪሞት ድረስ አላህን በመፍራት ላይ መሆን እንዳለበት።
5.     ከአላህ መከጀልን(መፈለግን) ማቋረጥ እንደሌለብን።
6.     ለሰው ብለን አምልኮን ከመስራት መቆጠብ እንዳለብን። ለሰው ብሎ የሚሰራ ስራው መጨረሻ ላይ እንደሚበላሽበት።
7.     ከ 4 ወር በፊት የወረደ ሰው እንዳልሆነ እና ከ 4 ወር ቡኋላ የወረደ ግን ልክ እንደ ማንኛውም ሙስሊም ተገንዞ፣ ሶላተል ጀናዛ ተሰግዶበት ሙስሊሞች ቀብር እንደሚቀበር።


Friday, May 30, 2014

Hadith ቁጥር 4 ‪ልብን ማጥራትና ስራን ማሳመር




Hadith ቁጥር 4

 
ከአቡ ሑረይራ እንደተዘገበው የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል ‹‹አላህ ወደመልካችሁና ወደ ገንዘቦቻችሁ አይመለከትም ነገር ግን ወደ ልቦቻችሁና ወደ ስራዎቻችሁ ይመለከታል ፡፡ (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል) 

1.ከሰዎች የሚፈለገው ትልቁ ነገር የፀዳ ልብና ያማረ ተግባር ነው፡፡
2.ልብን ማፅዳት ማለት ከሽርክ ፣ ከምቀኝነት ፣ በሰዎች ከመመካት ፣ ሙስሊምን ከመጥላትና ከመሳሰሉት የልብ በሽታዎች መጠበቅ ማለት ሲሆን ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ልብ ካማረ አካል ሙሉ ያምራል ብለዋል፡፡
3.ስራ ተቀባይነት የሚኖረው ለአላህ ብቻ ጥርት ተደርጎ ሲሰራና የነብዩን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) መመሪያ የተከተለ ሲሆን ብቻ ነው፡፡
4.መልካም ስራን ማብዛት አላህ ዘንድ ደረጃን ከፍ ያደርጋል፡፡
5.ሰዎች የሚለኩት በውበትና በገንዘብ ሳይሆን ለአላህ ባላቸው ፍራቻና መልካም ስራ ነው፡፡
6.አላህ ሀብት የሰጠው ሰው ሀብቱን በመልካም ነገር ላይ ካላዋለው አላህ ዘንድ ይጠየቅበታል፡፡
7.ሙስሊም ገንዘብ ስሌለለው መናቅ ወይም ገንዘቡ ብሎ ማክበር የሙስሊም ባህሪ አይደለም


የተወሰደ።

Tuesday, May 27, 2014

ከአርበዒን አን-ነወውያህ ሓዲሶች የምንወስዳቸው ትምህርቶች 2ኛ እና 3ኛ ሓዲስ የሃይማኖት ደረጃዎች።



2ኛ እና 3ኛ  ሓዲስ

የሃይማኖት ደረጃዎች።

ከሁለተኛው እና  ከሶስተኛው ሓዲስ የምንወስዳቸው ትምህርቶች

1.      ሙስሊሞች ጋር መቀላቀልና ለነሱ ደግሞ መልካም ባህርያትን ማሳየት እንዳለብን
2.     ሌሎች ሰዎችን ለማስተማር ብሎ ዓሊምን መጠየቅ እንደሚቻልና ይህንን ያደረገ ደግሞ ልክ እውቀቱን የሚያሰተላልፈው ሰው አጅር ያገኛል።
3.     እስልምና  አምስት ማእዘናት እንዳሉት። ካለነሱ ደግሞ ዲን እንደማይቆም።
4.     ኢማን ስድስት ማእዘናት እንዳሉት።
5.     እስልምናና ኢማን አብረው ሲጠቀሱ የተለያየ ትርጉም እንዳላቸው። ለየብቻቸው ሲጠቀሱ ግን አንደኛው ሌላኛውን አጠቃሎ እንደሚይዝ።
6.     የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ሶስት ደረጃዎች እንዳላቸው። እነሱም
ኢስላም(ሙስሊም)
ኢማን(ሙእሚን)
ኢሕሳን(ሙሕሲን)

7.     የውመል ቂያማ ሰአቷ የተወሰነ እንደሆነ እና እሷንም የሚያቃት አንድ አላህ ብቻ እንደሆነ። ምልክቶችም እንደላት።

Sunday, May 25, 2014

ከአርበዒን አን-ነወውያህ ሓዲሶች የምንወስዳቸው ትምህርቶች ሓዲስ 1ኛ

1ኛ  ሓዲስ

ስራ በንያ ነው የሚለካው።

ከአንደኛው ሓዲስ የምንወስዳቸው ትምህርቶች
1.      ሁሉም ስራ ንያ እንዳለው።
2.     ሁሉም ሰው በንያው መሰረት ስራው እንደሚመዘንለት።

3.     የሚያስተምር ሰው ምሳሌን እያጠቀሰ ቢያስተምር ጥሩ እንደሆነ።